1
ፊልጵስዩስ 4:6
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ፣ ከምስጋናም ጋር ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ እንጂ ስለ ማንኛውም ነገር አትጨነቁ።
Compare
Explore ፊልጵስዩስ 4:6
2
ፊልጵስዩስ 4:7
ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም፣ ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
Explore ፊልጵስዩስ 4:7
3
ፊልጵስዩስ 4:8
በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፤ እውነት የሆነውን ሁሉ፣ ክቡር የሆነውን ሁሉ፣ ትክክል የሆነውን ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ፣ መልካም የሆነውን ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ወይም ምስጋና እንደ እነዚህ ስላሉት ነገሮች አስቡ።
Explore ፊልጵስዩስ 4:8
4
ፊልጵስዩስ 4:13
ኀይልን በሚሰጠኝ በእርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ።
Explore ፊልጵስዩስ 4:13
5
ፊልጵስዩስ 4:4
ምንጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ።
Explore ፊልጵስዩስ 4:4
6
ፊልጵስዩስ 4:19
አምላኬም እንደ ታላቅ ባለጠግነቱ መጠን የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ይሞላባችኋል።
Explore ፊልጵስዩስ 4:19
7
ፊልጵስዩስ 4:9
ከእኔ የተማራችሁትን ወይም የተቀበላችሁትን፣ የሰማችሁትን ወይም ያያችሁትን ማናቸውንም ነገር አድርጉ፤ የሰላም አምላክም ከእናንተ ጋር ይሆናል።
Explore ፊልጵስዩስ 4:9
8
ፊልጵስዩስ 4:5
ገርነታችሁ በሁሉ ዘንድ የታወቀ ይሁን፤ ጌታ ቅርብ ነው።
Explore ፊልጵስዩስ 4:5
9
ፊልጵስዩስ 4:12
ማጣትን ዐውቀዋለሁ፤ ማግኘትንም ዐውቀዋለሁ። ብጠግብም ሆነ ብራብ፣ ባገኝም ሆነ ባጣ፣ በማንኛውም ሆነ በየትኛውም ሁኔታ ያለኝ ይበቃኛል የማለትን ምስጢር ተምሬአለሁ።
Explore ፊልጵስዩስ 4:12
10
ፊልጵስዩስ 4:11
ይህን የምለው ስለ ቸገረኝ አይደለም፤ ምክንያቱም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ያለኝ ይበቃኛል ማለትን፣
Explore ፊልጵስዩስ 4:11
Home
Bible
Plans
Videos