1
1 የጴጥሮስ መልእክት 5:7
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እርሱ ለእናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሐሳብ ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።
Compare
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 5:7
2
1 የጴጥሮስ መልእክት 5:10
ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ በክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብር የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ እርሱ ራሱ ከተቀበላችሁት መከራ ያድናችኋል፤ ይደግፋችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ይመሠርታችኋልም።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 5:10
3
1 የጴጥሮስ መልእክት 5:8-9
በመጠን ኑሩ፤ ንቁም! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙሪያችሁ ይንጐራደዳል። በዓለም ሁሉ ያሉ ወንድሞቻችሁ ይህን ዐይነት መከራ እንደሚቀበሉ በማወቅ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 5:8-9
4
1 የጴጥሮስ መልእክት 5:6
እንግዲህ እግዚአብሔር በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ ሥር ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 5:6
5
1 የጴጥሮስ መልእክት 5:5
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 5:5
Home
Bible
Plans
Videos