1
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:13
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ይቅር በሉ።
Compare
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:13
2
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:2
ዘወትር በላይ በሰማይ ስላሉት ነገሮች አስቡ እንጂ በምድር ላይ ስላሉት ነገሮች አታስቡ።
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:2
3
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:23
የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ ኢየሱስ እንደምታደርጉት ዐይነት ከልባችሁ አድርጉት።
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:23
4
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:12
እንግዲህ የእግዚአብሔር ምርጦችና ቅዱሳን፥ የተወደዳችሁም እንደ መሆናችሁ መጠን ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትሕትናን፥ ገርነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ።
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:12
5
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:16-17
የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ። በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት፤ በእርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑ።
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:16-17
6
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:14
ከዚህም ሁሉ በላይ ሁሉን ነገር ሰብስቦ በማሰር ፍጹም አንድነትን የሚያስገኘውን ፍቅርን ልበሱ።
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:14
7
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:1
እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከሞት ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ በሰማይ ያሉትን ነገሮች ፈልጉ።
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:1
8
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:15
የአንድ አካል ክፍሎች ሆናችሁ በእርግጥ የተጠራችሁት ለዚህ ሰላም ስለ ሆነ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገሥ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:15
9
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:5
ስለዚህ በእናንተ የሚገኙትን የምድራዊ ሕይወት ምኞቶች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም “ዝሙት፥ ርኲሰት፥ ፍትወት፥ ክፉ ምኞት፥ ጣዖት ማምለክ የሆነ መጐምጀት” ናቸው።
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:5
10
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:3
እናንተ በሞት የመለየትን ያኽል ከዚህ ዓለም ተለይታችኋል፤ ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ውስጥ ተሰውሮአል።
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:3
11
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:8
አሁን ግን ቊጣን፥ ንዴትን፥ ተንኰልን፥ ስም ማጥፋትን ከእናንተ አስወግዱ፤ የሚያሳፍር ንግግርም ከአፋችሁ አይውጣ።
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:8
12
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:9-10
አሮጌውን ባሕርይ ከነሥራው አውልቃችሁ ስለ ጣላችሁት እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ። በፈጣሪው አምሳል በዕውቀት እየታደሰ የሚሄደውን አዲሱን ባሕርይ ልበሱ።
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:9-10
13
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:19
ባሎች ሆይ! ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ ጨካኞችም አትሁኑባቸው።
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:19
14
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:20
ልጆች ሆይ! ይህ ጌታን ደስ የሚያሰኝ ስለ ሆነ በሁሉ ነገር ለወላጆቻችሁ ታዘዙ።
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:20
15
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:18
ሚስቶች ሆይ! በጌታ ዘንድ ተገቢ ስለ ሆነ ለባሎቻችሁ ታዘዙ።
Explore ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:18
Home
Bible
Plans
Videos