1
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:5
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ከገንዘብ ፍቅር ራቁ፤ ያላችሁ ይብቃችሁ፤ እግዚአብሔር “ከቶ አልጥልህም፤ ፈጽሞም አልተውህም” ብሎአል።
Compare
Explore ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:5
2
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:8
ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትም ዛሬም ለዘለዓለምም ያው ነው፤ አይለወጥም።
Explore ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:8
3
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:6
ስለዚህ በመተማመን፥ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።
Explore ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:6
4
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:16
መልካም ነገር ማድረግንና ያላችሁን ነገር ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ፤ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ እንዲህ ያለው መሥዋዕት ነው።
Explore ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:16
5
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:15
እንግዲህ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የምስጋና መሥዋዕት ዘወትር ለእግዚአብሔር እናቅርብ፤ ይህም ስለ ስሙ በሚመሰክሩት ከንፈሮች የሚቀርብ የምስጋና መሥዋዕት ነው።
Explore ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:15
6
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:4
ጋብቻ በሁሉ ዘንድ የተከበረ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን እግዚአብሔር ስለሚፈርድባቸው ባልና ሚስት ታማኝነትን በማጒደል ጋብቻን አያርክሱ።
Explore ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:4
7
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:2
እንግዳ ተቀብሎ ማስተናገድን አትርሱ፤ እንደዚህ እንግዶችን እየተቀበሉ በማስተናገድ አንዳንድ ሰዎች ሳያውቁ መላእክትን ተቀብለው አስተናግደዋል።
Explore ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:2
8
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:20-21
ታላቁን የበጎች እረኛ ጌታችንን ኢየሱስን በዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ደም ከሞት ያስነሣው የሰላም አምላክ ፈቃዱን ለመፈጸም እንድትበቁ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ ደስ የሚያሰኘውንም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእኛ ያድርግ፤ ለኢየሱስ ክርስቶስም ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
Explore ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:20-21
Home
Bible
Plans
Videos