1
ትንቢተ ኢሳይያስ 35:10
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እግዚአብሔር የታደጋቸው ሰዎች ተመልሰው ይመጣሉ፤ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘወትር የደስታን ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ከእነርሱ ይርቃል።
Compare
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 35:10
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 35:3-4
የደከሙትን ክንዶች አጠንክሩ፥ የተብረከረኩ ጒልበቶችንም አጽኑ። ፈሪ ልብ ላላቸው “እነሆ አምላካችሁ ጠላቶቻችሁን ለመበቀልና የበደላቸውንም ዋጋ ለመክፈል መጥቶ ስለሚያድናችሁ በርቱ! አትፍሩ!” በሉአቸው።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 35:3-4
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 35:8
በዚያ “ቅዱስ ጐዳና” የሚባል መንገድ ይኖራል፤ እርሱም ለእግዚአብሔር ሰዎች ይሆናል፤ ንጹሕ ያልሆነ ሰው በዚያ መንገድ አይሄድም፤ ሞኞችም ሊሄዱበት አይችሉም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 35:8
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 35:5
በዚያን ጊዜ ዕውሮች ያያሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 35:5
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 35:6
አንካሶች እንደ ሚዳቋ ይዘላሉ፤ መናገር የማይችሉ ድዳዎች ይዘምራሉ፤ በበረሓ ውስጥ የጅረት ውሃ ይፈስሳል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 35:6
Home
Bible
Plans
Videos