ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ብዬ እንድናገር አዘዘኝ፦ “እነሆ አድምጡ! እኔ እግዚአብሔር ወደ ሕይወት የሚወስደውንና ወደ ሞት የሚያደርሰውን መንገድ በፊታችሁ አኑሬአለሁ፤ ከሁለቱ አንዱን ምረጡ፤ በዚህች ከተማ የሚቀሩ ሁሉ በጦርነት ወይም በራብ፥ ወይም በወረርሽኝ ይሞታሉ፤ አሁን ከተማይቱን ከበው ወዳሉት ወደ ባቢሎናውያን ሄዶ እጁን የሚሰጥ ግን አይሞትም፤ ሌላው ቢቀር ሕይወቱን ያተርፋል፤