1
የማቴዎስ ወንጌል 16:24
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ “እኔን መከተል የሚፈልግ ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።
Compare
Explore የማቴዎስ ወንጌል 16:24
2
የማቴዎስ ወንጌል 16:18
እኔም እንዲህ እልሃለሁ፤ አንተ (ጴጥሮስ)፥ አለት ነህ፤ በዚህችም የመሠረት ድንጋይ ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ ይህችንም ቤተ ክርስቲያን የሞት ኀይል እንኳ አያሸንፋትም።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 16:18
3
የማቴዎስ ወንጌል 16:19
እነሆ፥ ለአንተ የሰማይ መንግሥትን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሆናል።”
Explore የማቴዎስ ወንጌል 16:19
4
የማቴዎስ ወንጌል 16:25
ሕይወቱን ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፤ ሕይወቱን ስለ እኔ የሚያጠፋት ግን ያገኛታል።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 16:25
5
የማቴዎስ ወንጌል 16:26
ሰው የዓለሙን ሁሉ ሀብት ቢያገኝ፥ ነፍሱን ግን ቢያጠፋ፥ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ዋጋ ሊከፍል ይችላል?
Explore የማቴዎስ ወንጌል 16:26
6
የማቴዎስ ወንጌል 16:15-16
ኢየሱስም “እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው። በዚያን ጊዜ ስምዖን ጴጥሮስ፦ “አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ መሲሕ ነህ፤” ሲል መለሰለት።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 16:15-16
7
የማቴዎስ ወንጌል 16:17
ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! የተባረክህ ነህ! ይህን የገለጠልህ በሰማይ ያለው አባቴ ነው እንጂ ሰው አይደለም።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 16:17
Home
Bible
Plans
Videos