1
የማቴዎስ ወንጌል 6:33
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እናንተ ግን፥ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ የቀረው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል፤
Compare
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:33
2
የማቴዎስ ወንጌል 6:34
ነገ ለራሱ ይጨነቃል፤ ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።”
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:34
3
የማቴዎስ ወንጌል 6:25
ስለዚህ እንዲህ እላችኋለሁ፤ ‘ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ በማለት ስለ ኑሮአችሁ አትጨነቁ፤ ከምግብ ሕይወት፥ ከልብስም ሰውነት አይበልጥምን?
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:25
4
የማቴዎስ ወንጌል 6:6
አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ ክፍልህ ገብተህ፥ በርህን ዝጋና በስውር ወዳለው ወደማይታይ አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተሠራውን የሚያይ አባትህም የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:6
5
የማቴዎስ ወንጌል 6:9-10
ስለዚህ እናንተ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፦ ‘በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ! ስምህ ይመስገን፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነ፥ እንዲሁም በምድር ይሁን።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:9-10
6
የማቴዎስ ወንጌል 6:11
የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:11
7
የማቴዎስ ወንጌል 6:12
እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል፥ በደላችንን ይቅር በለን፤
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:12
8
የማቴዎስ ወንጌል 6:13
ከክፉ አድነን እንጂ፥ ወደ ፈተና አታግባን፤ [መንግሥት፥ ኀይልና ክብር ለዘለዓለም ያንተ ነው፤ አሜን።’]
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:13
9
የማቴዎስ ወንጌል 6:14
“የሰዎችን በደል ይቅር ብትሉላቸው፥ እናንተንም የሰማዩ አባታችሁ ይቅር ይልላችኋል።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:14
10
የማቴዎስ ወንጌል 6:26
እስቲ በሰማይ ላይ ወደሚበሩት ወፎች ተመልከቱ፤ እነርሱ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራ አይከቱም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:26
11
የማቴዎስ ወንጌል 6:19-21
ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ብልና ዝገት በሚያጠፉበት፥ ሌቦችም ሰብረው በሚሰርቁበት፥ በዚህ ምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ። ይልቅስ ብልና ዝገት ሊያጠፉት በማይችሉበት፥ ሌቦችም ሰብረው በማይሰርቁበት በሰማይ ሀብታችሁን አከማቹ። ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያ ይገኛል።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:19-21
12
የማቴዎስ ወንጌል 6:24
“አንድ ሰው ለሁለት ጌቶች አገልጋይ ሊሆን አይችልም፤ ወይም አንዱን ይጠላል፥ ሌላውንም ይወዳል፤ ወይም አንዱን ያከብራል፥ ሌላውን ይንቃል፤ እንዲሁም አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ አገልጋይ መሆን አይችልም።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:24
13
የማቴዎስ ወንጌል 6:30
ታዲያ ዛሬ ታይቶ ነገ በእሳት ውስጥ የሚጣለውን የሜዳ ሣር፥ እግዚአብሔር እንዲህ የሚያለብስ ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጐደላችሁ! እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁም!
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:30
14
የማቴዎስ ወንጌል 6:3-4
አንተ ግን ምጽዋት ስትመጸውት ቀኝ እጅህ የሚያደርገውን ግራ እጅህ አይወቅ። እንግዲህ ምጽዋትህ በስውር ይሁን፤ በስውር የተሠራውን የሚያየው አባትህ፥ የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:3-4
15
የማቴዎስ ወንጌል 6:1
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ሰዎች ይዩልን ብላችሁ መልካም ሥራችሁን በሰዎች ፊት ከማድረግ ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ ግን፥ በሰማይ አባታችሁ ዘንድ ምንም ዋጋ አታገኙም።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:1
16
የማቴዎስ ወንጌል 6:16-18
ኢየሱስም ቀጥሎ እንዲህ አለ፦ “በምትጾሙበት ጊዜ፥ መጾማቸውን ሰዎች እንዲያውቁላቸው፥ ፊታቸውን እንደሚለውጡት እንደ ግብዞች፥ ፊታችሁን አታጠውልጉ፤ በእውነት እላችኋለሁ፥ እነርሱ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን በምትጾምበት ጊዜ ፊትህን ታጠብ፤ ራስህንም ተቀባ፤ በዚህ አኳኋን፥ መጾምህን በስውር ካለው አባትህ በቀር ሌላ ማንም አያውቅም። በስውር የተሠራውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል።”
Explore የማቴዎስ ወንጌል 6:16-18
Home
Bible
Plans
Videos