1
የዮሐንስ ራእይ 11:15
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ሰባተኛውም መልአክ እምቢልታውን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት የጌታ የአምላካችንና የመሲሑ ሆናለች፤ እርሱ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤” የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ።
Compare
Explore የዮሐንስ ራእይ 11:15
2
የዮሐንስ ራእይ 11:18
አሕዛብ ተቈጡ፤ የአንተም ቊጣ መጣ፤ ሙታን ፍርድ የሚያገኙበት ጊዜም ደረሰ፤ ለአገልጋዮችህ ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚያከብሩት፥ ለታናናሾችና ለታላላቆች፥ ዋጋቸውን የምትሰጥበት ጊዜ ደረሰ፤ ምድርን ያጠፉአትን የምታጠፋበት ጊዜም ደረሰ።”
Explore የዮሐንስ ራእይ 11:18
3
የዮሐንስ ራእይ 11:3
ሁለቱ ምስክሮቼ የሐዘን ልብስ ለብሰው አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሥልሳ ቀን ትንቢት እንዲናገሩ ኀይል እሰጣቸዋለሁ።”
Explore የዮሐንስ ራእይ 11:3
4
የዮሐንስ ራእይ 11:11
ነገር ግን ሦስት ቀን ተኩል ካለፈ በኋላ ሕይወት የሚሰጥ እስትንፋስ ከእግዚአብሔር መጥቶ ወደ ሬሳዎቹ ገባ፤ በእግራቸውም ቆሙ፤ ያዩአቸውም ሰዎች እጅግ ፈሩ።
Explore የዮሐንስ ራእይ 11:11
5
የዮሐንስ ራእይ 11:6
እነርሱ ትንቢት በሚናገሩባቸው በእነዚህ ቀኖች ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ለመዝጋት ሥልጣን አላቸው፤ እንዲሁም ውሃዎችን ወደ ደም ለመለወጥና በሚፈልጉትም ጊዜ ሁሉ በማንኛውም ዐይነት መቅሠፍት ምድርን ለመምታት ሥልጣን አላቸው።
Explore የዮሐንስ ራእይ 11:6
6
የዮሐንስ ራእይ 11:4-5
እነርሱ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ የወይራ ዛፎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው፤ ማንም እነርሱን ሊጐዳ ቢፈልግ እሳት ከአፋቸው ወጥቶ ጠላቶቻቸውን ያቃጥላል፤ እነርሱን ሊጐዳ የሚፈልግ ሁሉ የሚሞተው በዚህ ዐይነት ነው።
Explore የዮሐንስ ራእይ 11:4-5
Home
Bible
Plans
Videos