1
የዮሐንስ ራእይ 3:20
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እነሆ! እኔ በበር ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ሰምቶ በሩን ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ ገብቼ ከእርሱ ጋር እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል፤
Compare
Explore የዮሐንስ ራእይ 3:20
2
የዮሐንስ ራእይ 3:15-16
ሥራህን ዐውቃለሁ፤ ቀዝቃዛ ወይም ትኩስ አይደለህም፤ ቀዝቃዛ ወይም ትኩስ ብትሆን ኖሮ መልካም በሆነ ነበር! ቀዝቃዛ ወይም ትኩስ ሳትሆን ለብ ያልክ ስለ ሆንክ ከአፌ አውጥቼ ልተፋህ ነው፤
Explore የዮሐንስ ራእይ 3:15-16
3
የዮሐንስ ራእይ 3:19
እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸዋለሁም፤ ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ፤
Explore የዮሐንስ ራእይ 3:19
4
የዮሐንስ ራእይ 3:8
ሥራህን ዐውቃለሁ፤ እነሆ፥ ማንም ሊዘጋው የማይችለውን የተከፈተ በር በፊትህ አድርጌልሃለሁ፤ ኀይልህ ትንሽ መሆኑን ዐውቃለሁ፤ ይሁን እንጂ ቃሌን ጠብቀሃል፤ ስሜንም አልካድክም።
Explore የዮሐንስ ራእይ 3:8
5
የዮሐንስ ራእይ 3:21
እኔ ድል ነሥቼ ከአባቴ ጋር በዙፋኑ ላይ እንደ ተቀመጥኩ እንዲሁም ድል የነሣ ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ።
Explore የዮሐንስ ራእይ 3:21
6
የዮሐንስ ራእይ 3:17
‘እኔ ሀብታም ነኝ፤ ብዙ ሀብት አለኝ፤ የሚጐድለኝ ምንም የለም’ ትላለህ፤ ነገር ግን ጐስቋላ፥ ምስኪን፥ ድኻ፥ ዕውርና የተራቈትህ መሆንክን አታውቅም፤
Explore የዮሐንስ ራእይ 3:17
7
የዮሐንስ ራእይ 3:10
ትዕግሥተኛ ሁን ያልኩህን ቃሌን ስለ ጠበቅህ እኔም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሊፈትናቸው በዓለም ሁሉ ላይ ከሚመጣው ከመከራ ሰዓት እጠብቅሃለሁ።
Explore የዮሐንስ ራእይ 3:10
8
የዮሐንስ ራእይ 3:11
እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፤ አክሊልህን ማንም እንዳይወስድብህ ያለህን አጥብቀህ ያዝ።
Explore የዮሐንስ ራእይ 3:11
9
የዮሐንስ ራእይ 3:2
ንቃ፤ ሊሞት የተቃረበውንና የቀረልህን ትንሽ ኀይል አጠናክር፤ በአምላኬ ፊት ሥራህን ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትም።
Explore የዮሐንስ ራእይ 3:2
Home
Bible
Plans
Videos