1
ወደ ሮም ሰዎች 12:2
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
መልካሙንና ደስ የሚያሰኘውን ፍጹም የሆነውንም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ እንድትችሉ አእምሮአችሁን በማደስ ሕይወታችሁ ይለወጥ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉት።
Compare
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:2
2
ወደ ሮም ሰዎች 12:1
እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:1
3
ወደ ሮም ሰዎች 12:12
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ጊዜ ታገሡ፤ ሁልጊዜ ጸልዩ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:12
4
ወደ ሮም ሰዎች 12:21
ስለዚህ ክፉውን ነገር በመልካም ነገር አሸንፍ እንጂ በክፉ ነገር አትሸነፍ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:21
5
ወደ ሮም ሰዎች 12:10
እርስ በርሳችሁ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ለመከባበርም ተሽቀዳደሙ፤
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:10
6
ወደ ሮም ሰዎች 12:9
ግብዝነት የሌለበት እውነተኛ ፍቅር ይኑራችሁ፤ ክፉውን ነገር ጥሉ፤ መልካሙን ነገር ተከተሉ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:9
7
ወደ ሮም ሰዎች 12:18
የሚቻላችሁ ቢሆን ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር በእናንተ በኩል የሚያስፈልገውን ሁሉ አድርጉ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:18
8
ወደ ሮም ሰዎች 12:19
ወዳጆቼ ሆይ! ቊጣን ለእግዚአብሔር ተዉ እንጂ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ “የምበቀልና የበቀልንም ብድራት የምከፍል እኔ ነኝ ይላል ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአል።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:19
9
ወደ ሮም ሰዎች 12:11
ሳትታክቱ የጋለ መንፈስን ተከትላችሁ ጌታን አገልግሉ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:11
10
ወደ ሮም ሰዎች 12:3
ደግሞም እያንዳንዳችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ እምነት መጠን በትሕትና አስቡ እንጂ ከሚገባችሁ በላይ ስለ ራሳችሁ በትዕቢት አታስቡ ብዬ በተሰጠኝ ጸጋ እነግራችኋለሁ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:3
11
ወደ ሮም ሰዎች 12:17
በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር አድርጉ እንጂ፥ ሰዎች ክፉ ነገር ሲያደርጉባችሁ፥ እናንተም መልሳችሁ ክፉ ነገር አታድርጉባቸው።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:17
12
ወደ ሮም ሰዎች 12:16
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማምታችሁ ኑሩ፤ ራሳችሁን ከፍ ከማድረግ ይልቅ ትዕቢትን አስወግዳችሁ ከድኾች ጋር በአንድነት ኑሩ፤ በራሳችሁ ዐዋቂዎች ነን አትበሉ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:16
13
ወደ ሮም ሰዎች 12:20
ስለዚህ ከመበቀል ይልቅ ጠላትህን ቢርበው አብላው፤ ቢጠማውም አጠጣው፤ ይህን ብታደርግ በዕፍረት እሳት ታቃጥለዋለህ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:20
14
ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15
የሚያሳድዱአችሁንም መርቁ፤ መርቁአቸው እንጂ አትርገሙአቸው። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15
15
ወደ ሮም ሰዎች 12:13
አማኞች ወንድሞችን በችግራቸው እርዱ፤ በእንግድነት የሚመጡትንም ተቀበሉ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:13
16
ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5
በአንዱ አካላችን ብዙ ክፍሎች አሉ፤ እያንዳንዱም የአካል ክፍል የተለየ ሥራ አለው። እንዲሁም እኛ ብዙዎች ሆነን ሳለ በክርስቶስ አንድ አካል ነን፤ የአንድ አካል ክፍሎች እንደ መሆናችንም እርስ በርሳችን ተጣምረናል።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5
Home
Bible
Plans
Videos