1
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:19-20
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ወይስ ሰውነታችሁ፥ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት፥ በውስጣችሁም የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆኑን አታውቁም? እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም። በዋጋ ተገዝታችኋል፤ ስለዚህ በሰውነታችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።
Compare
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:19-20
2
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:9-10
ወይስ ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አትሳሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥ ወይም ሌቦች ወይም ስግብግቦች ወይም ሰካራሞች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:9-10
3
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:18
ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሰውነቱ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሰውነቱ ላይ ኃጢአትን ይሠራል።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:18
4
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:12
“ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤” ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:12
5
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:14
እግዚአብሔርም ጌታን ከሞት አስነሣ፥ እኛንም በኀይሉ ያስነሣናል።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:14
Home
Bible
Plans
Videos