1
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:6-7
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ፤ አብዝታችሁ ምስጋናን በማቅረብ እንደ ተማራችሁት ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፤ በእምነትም ጽኑ።
Compare
Explore ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:6-7
2
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:8
እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን እንደ ሰው ወግና እንደ መሠረታዊው የዓለም ረቂቅ መንፈስ በፍልስፍናና በከንቱ መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠንቀቁ።
Explore ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:8
3
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:13-14
እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሞታችሁ የነበራችሁትን በደላችንን ሁሉ ይቅር ባለን ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ፤ እርሱም ይፃረረንና ይቃወመን የነበረውን በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ በመስቀልም ላይ ቸንክሮ ከእኛ አስወገደው፤
Explore ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:13-14
4
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:9-10
በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል ተገልጦ ይኖራልና፤ የአለቅነትና የሥልጣን ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል።
Explore ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:9-10
5
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:16-17
እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ፤ እነዚህ ወደ ፊት ለሚመጡት ነገሮች እንደ ጥላ ናቸውና፤ እውነቱ የሚገኘው ግን በክርስቶስ ነው።
Explore ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:16-17
Home
Bible
Plans
Videos