1
ወደ ዕብራውያን 10:25
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
አንዳንዶችም ልምድ አድርገው እንደያዙት፥ መሰብሰባችንን አንተው፤ እርስ በርሳችን እንመካከር፤ ይልቁንም የቀኑን መቅረብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።
Compare
Explore ወደ ዕብራውያን 10:25
2
ወደ ዕብራውያን 10:24
ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተሳሰብ፤
Explore ወደ ዕብራውያን 10:24
3
ወደ ዕብራውያን 10:23
የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና፥ ተስፋ የሚሰጠንን ምስክርነት ያለመናወጥ በጽናት እንጠብቅ፤
Explore ወደ ዕብራውያን 10:23
4
ወደ ዕብራውያን 10:36
የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ ጽናት ያስፈልጋችኋል።
Explore ወደ ዕብራውያን 10:36
5
ወደ ዕብራውያን 10:22
ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተንና ሰውነታችንን በንጹህ ውሃ ታጥበን፥ በቅን ልብ በፍጹም እምነት እንቅረብ፤
Explore ወደ ዕብራውያን 10:22
6
ወደ ዕብራውያን 10:35
ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ።
Explore ወደ ዕብራውያን 10:35
7
ወደ ዕብራውያን 10:26-27
የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርብልንም፤ ነገር ግን የሚያስፈራ የፍርድና ተቃዋሚዎችንም ለመብላት የሚጠብቅ የእሳት ግለት አለ።
Explore ወደ ዕብራውያን 10:26-27
Home
Bible
Plans
Videos