1
ወደ ዕብራውያን 12:1-2
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
እንግዲህ እነደዚህ ዓይነት ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ማንኛውንም ሸክምና የተጣበቅንበትን ኅጢአት ሁሉ አራግፈን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ። የእምነታችንንም ራስና ፍጽምና የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፥ ውርደቱንም ንቆ፥ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።
Compare
Explore ወደ ዕብራውያን 12:1-2
2
ወደ ዕብራውያን 12:11
ለጊዜው ቅጣት ሁሉ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰላማዊ የጽድቅን ፍሬ ያፈራላቸዋል።
Explore ወደ ዕብራውያን 12:11
3
ወደ ዕብራውያን 12:14
ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር ጣሩ፤ ያለ ቅድስናም ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና ለመቀደስም ፈልጉ።
Explore ወደ ዕብራውያን 12:14
4
ወደ ዕብራውያን 12:3
በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኀጢአተኞች የደረሰበትን እንዲህ ያለውን ተቃውሞ እንዴት እንደተቋቋመ አስቡ።
Explore ወደ ዕብራውያን 12:3
5
ወደ ዕብራውያን 12:28
ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤
Explore ወደ ዕብራውያን 12:28
6
ወደ ዕብራውያን 12:7
እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፥ የተግሣጽን ቅጣት ታገሡ፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?
Explore ወደ ዕብራውያን 12:7
7
ወደ ዕብራውያን 12:29
አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።
Explore ወደ ዕብራውያን 12:29
8
ወደ ዕብራውያን 12:10
እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበር፤ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል።
Explore ወደ ዕብራውያን 12:10
9
ወደ ዕብራውያን 12:4
ከኃጢአት ጋር በምታደርጉት ተጋድሎ ገና ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም፤
Explore ወደ ዕብራውያን 12:4
Home
Bible
Plans
Videos