1
የማቴዎስ ወንጌል 22:37-39
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
እርሱም እንዲህ አለው “‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ።’ ታላቂቱና የመጀመሪያይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርሷም ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤’ የምትለው ናት።
Compare
Explore የማቴዎስ ወንጌል 22:37-39
2
የማቴዎስ ወንጌል 22:40
በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕግና ነቢያት ሁሉ ተንጠልጥለዋል።”
Explore የማቴዎስ ወንጌል 22:40
3
የማቴዎስ ወንጌል 22:14
የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።”
Explore የማቴዎስ ወንጌል 22:14
4
የማቴዎስ ወንጌል 22:30
በሙታን ትንሣኤ ጊዜ እንደ መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም ወይም አይጋቡም።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 22:30
5
የማቴዎስ ወንጌል 22:19-21
ለግብር የሚከፈለውን ብር አሳዩኝ።” እነርሱም ዲናር አመጡለት። እርሱም “ይህ መልክና ጽሑፉ የማን ነው?” አላቸው። እነርሱም “የቄሣር ነው” አሉት። እርሱም “እንግዲያውስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ” አላቸው።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 22:19-21
Home
Bible
Plans
Videos