1
ወደ ጢሞቴዎስ 1 4:11-12
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው።
Compare
Explore ወደ ጢሞቴዎስ 1 4:11-12
2
ወደ ጢሞቴዎስ 1 4:8
ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።
Explore ወደ ጢሞቴዎስ 1 4:8
3
ወደ ጢሞቴዎስ 1 4:16
ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።
Explore ወደ ጢሞቴዎስ 1 4:16
4
ወደ ጢሞቴዎስ 1 4:1-2
መንፈስ ግን በግልጥ “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ፤” ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥
Explore ወደ ጢሞቴዎስ 1 4:1-2
5
ወደ ጢሞቴዎስ 1 4:7
ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።
Explore ወደ ጢሞቴዎስ 1 4:7
6
ወደ ጢሞቴዎስ 1 4:13
እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም ተጠንቀቅ።
Explore ወደ ጢሞቴዎስ 1 4:13
Home
Bible
Plans
Videos