1
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:6-7
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እንግዲህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ተቀበላችሁት፥ በእርሱ ተመላለሱ። በእርሱ ተመሥርታችሁ ታነጹ፤ በምስጋናው ትበዙ ዘንድ፥ በተማራችሁት ሃይማኖት ጽኑ።
Compare
Explore ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:6-7
2
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:8
ለዚህ ዓለም ስሕተት፥ በክርስቶስ ሕግ ያይደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥርዐት ለከንቱ የሚያታልሉ ሰዎች በነገር ማራቀቅ እንዳያታልሉአችሁ፥ ተጠንቀቁ።
Explore ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:8
3
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:13-14
እናንተም በኀጢአታችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን ነበራችሁና፥ ከእርሱ ጋር ሕያዋን አደረጋችሁ፤ ኀጢአታችሁንም ሁሉ ይቅር አላችሁ። ከባላጋራችን የተነሣ በትእዛዝ የተጻፈውን የዕዳችንን ደብዳቤ ደመሰሰልን፤ ከመካከላችንም አራቀው፤ በመስቀሉም ቸነከረው።
Explore ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:13-14
4
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:9-10
በእርሱ ፍጹም መለኮቱ በሥጋ ተገልጦ ይኖራልና። እናንተም በእርሱ ፍጹማን ሁኑ፤ እርሱ ለአለቅነት ሁሉና ለሥልጣን ሁሉ ራስ ነውና።
Explore ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:9-10
5
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:16-17
እንግዲህ በመብልም ቢሆን፥ በመጠጥም ቢሆን፥ በልዩ ልዩ በዓላትም ቢሆን፥ በመባቻም ቢሆን፥ በሰንበትም ቢሆን የሚነቅፋችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ። ይህ ሁሉ ይመጣ ዘንድ ላለው ጥላ ነውና። አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።
Explore ወደ ቈላስይስ ሰዎች 2:16-17
Home
Bible
Plans
Videos