1
ወደ ዕብራውያን 13:5
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ገንዘብ ሳትወዱ ኑሩ፤ ያላችሁም ይበቃችኋል፤ እርሱ “አልጥልህም፤ ቸልም አልልህም” ብሎአልና።
Compare
Explore ወደ ዕብራውያን 13:5
2
ወደ ዕብራውያን 13:8
ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትናና ዛሬ እስከ ዘለዓለም የሚኖር እርሱ ነውና።
Explore ወደ ዕብራውያን 13:8
3
ወደ ዕብራውያን 13:6
አሁንም አምነን፥ “እግዚአብሔር ይረዳኛል፥ አልፈራም፥ ሰው ምን ያደርገኛል?” እንበል።
Explore ወደ ዕብራውያን 13:6
4
ወደ ዕብራውያን 13:16
ነገር ግን ለድሆች መራራትን፥ ከእነርሱም ጋር መተባበርን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።
Explore ወደ ዕብራውያን 13:16
5
ወደ ዕብራውያን 13:15
በውኑ እንግዲህ በስሙ እናምን ዘንድ የከንፈሮቻችን ፍሬ የሚሆን የምስጋና መሥዋዕትን በየጊዜው ለእግዚአብሔር ልናቀርብ አይገባንምን?
Explore ወደ ዕብራውያን 13:15
6
ወደ ዕብራውያን 13:4
መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመኝታቸውም ርኵሰት የለውም፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።
Explore ወደ ዕብራውያን 13:4
7
ወደ ዕብራውያን 13:2
እንግዳ መቀበልንም አትርሱ፤ በዚህ ምክንያት ሳያውቁ መላእክትን በእንግድነት ለመቀበል ያታደሉ አሉና።
Explore ወደ ዕብራውያን 13:2
8
ወደ ዕብራውያን 13:20-21
በዘለዓለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው፥ የሰላም አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘለዓለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
Explore ወደ ዕብራውያን 13:20-21
Home
Bible
Plans
Videos