1
ትንቢተ ኢሳይያስ 42:6-7
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
“እኔ እግዚአብሔር አምላክ በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፤ በእጄም እይዝሃለሁ፤ አበረታሃለሁም፤ ለልጅ ልጅ ቃል ኪዳን፥ ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ። የዕውራንንም ዐይን ትከፍት ዘንድ፥ የተጋዙትንም ከግዞት ቤት፥ በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ።
Compare
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 42:6-7
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 42:8
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 42:8
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 42:1
እነሆ፥ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ ያዕቆብ፤ ነፍሴ የተቀበለችው ምርጤ እስራኤልም፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያመጣል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 42:1
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 42:3-4
የተቀጠቀጠ ሸንበቆን አይሰብርም፤ የሚጤስንም ክር አያጠፋም፤ ነገር ግን በእውነት ፍርድን ያመጣል። በምድርም ፍርድን እስኪያደርግ ድረስ ያበራል እንጂ አይጠፋም፤ አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 42:3-4
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 42:16
ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ የማያውቋትንም ጎዳና እንዲረግጡ አደርጋቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህንም አደርግላቸዋለሁ፤ አልተዋቸውምም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 42:16
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 42:9
እነሆ የቀድሞው ነገር ተፈጸመ፤ አዲስ ነገርንም እናገራለሁ፤ አስቀድሞም ሳይነገር እርሱን አስታውቃችኋለሁ።”
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 42:9
Home
Bible
Plans
Videos