1
ኦሪት ዘዳግም 6:5
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ።
Compare
Explore ኦሪት ዘዳግም 6:5
2
ኦሪት ዘዳግም 6:7
ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው።
Explore ኦሪት ዘዳግም 6:7
3
ኦሪት ዘዳግም 6:6
እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 6:6
4
ኦሪት ዘዳግም 6:4
እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤
Explore ኦሪት ዘዳግም 6:4
5
ኦሪት ዘዳግም 6:8
በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 6:8
6
ኦሪት ዘዳግም 6:9
በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው።
Explore ኦሪት ዘዳግም 6:9
7
ኦሪት ዘዳግም 6:13
አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፤ እርሱንም አምልክ፤ በስሙም ማል።
Explore ኦሪት ዘዳግም 6:13
8
ኦሪት ዘዳግም 6:10-12
አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ባገባህ ጊዜ፤ ያልሠራሃቸውንም ታላቅና መልካም ከተሞች፥ ያልሞላሃቸውንም ሀብትን የሞሉ ቤቶች፥ ያልማስሃቸውንም የተማሱ ጉድጉዶች፥ ያልተከልሃቸውንም ወይንና ወይራ በሰጠህ ጊዜ፥ በበላህና በጠገብህም ጊዜ፤ በዚያን ጊዜ ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 6:10-12
9
ኦሪት ዘዳግም 6:1-2-1-2
አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም በዕድሜአችሁ ሁሉ ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር ታደርጉአት ዘንድ፥ አምላክህን እግዚአብሔርን ፈርተህ እኔ ለአንተ ያዘዝሁትን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንዳስተምራችሁ ያዘዛት ትእዛዝና ሥርዓት ፍርድም ይህች ናት።
Explore ኦሪት ዘዳግም 6:1-2-1-2
10
ኦሪት ዘዳግም 6:18-19
መልካምም ይሆንልህ ዘንድ፥ እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብተህ እርስዋን ትወርስ ዘንድ፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ ያወጣልህ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ፊት ቅኑንና መልካሙን አድርግ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 6:18-19
11
ኦሪት ዘዳግም 6:14-15
በመካከልህ ያለው አምላክህ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነውና የአምላክህ የእግዚአብሔር ቁጣ እንዳይነድድብህ ከምድርም ፊት እንዳያጠፋህ፥ በዙሪያችሁ ያሉት አሕዛብ የሚያመልኩአቸውን ሌሎችን አማልክት አትከተሉ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 6:14-15
12
13
ኦሪት ዘዳግም 6:16
በማሳህ እንደ ፈተናችሁት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አትፈታተኑት።
Explore ኦሪት ዘዳግም 6:16
Home
Bible
Plans
Videos