1
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:32
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።
Compare
Explore ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:32
2
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:2
በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤
Explore ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:2
3
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:29
ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።
Explore ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:29
4
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:31
መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።
Explore ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:31
5
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:26-27
ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።
Explore ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:26-27
6
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:22-24
ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።
Explore ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:22-24
7
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:3
በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።
Explore ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:3
8
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:11-12-13
እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።
Explore ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:11-12-13
9
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:14-15
እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥ ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤
Explore ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:14-15
Home
Bible
Plans
Videos