1
ትንቢተ ኢሳይያስ 11:2-3
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል። እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፥
Compare
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 11:2-3
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 11:1
ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 11:1
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 11:4
ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፥ በአፉም በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 11:4
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 11:5
የወገቡ መታጠቂያ ጽድቅ፥ የጎኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 11:5
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 11:9
በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ አይጐዱም አያጠፉምም፥ ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 11:9
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 11:6
ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል፥ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል፥ ጥጃና የአንበሳ ደቦል ፍሪዳም በአንድነት ያርፋሉ፥ ታናሽም ልጅ ይመራቸዋል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 11:6
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 11:10
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ለአሕዛብ ምልክት ሊሆን የቆመውን የእሴይን ሥር አሕዛብ ይፈልጉታል፥ ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 11:10
Home
Bible
Plans
Videos