1
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:17
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፥ በፍርድም የሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር።
Compare
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:17
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:10
ተራሮች ይፈልሳሉ፥ ኮረብቶችም ይወገዳሉ፥ ቸርነቴ ግን ከአንቺ ዘንድ አይፈልስም የሰላሜም ቃል ኪዳን አይወገድም፥ ይላል መሐሪሽ እግዚአብሔር።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:10
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:4
አታፍሪምና አትፍሪ፥ አትዋረጂምና አትደንግጪ፥ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፥ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:4
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:5
ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፥ የእስራኤልም ቅዱስ ታዳጊሽ ነው፥ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:5
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:2
የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፥ አትቈጥቢ፥ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:2
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:13
ልጆችሽም ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፥ የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:13
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:8
በጥቂት ቍጣ ለቅጽበተ ዓይን ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፥ በዘላለምም ቸርነት እምርሻለሁ፥ ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:8
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:7
ጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፥ በታላቅም ምሕረት እሰበስብሻለሁ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:7
9
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:9
ይህ ለኔ እንደ ኖኅ ውኃ ነው፥ የኖኅ ውኃ ደግሞ በምድር ላይ እንዳያልፍ እንደ ማልሁ፥ እንዲሁ አንቺን እንዳልቈጣ እንዳልዘልፍሽም ምያለሁ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:9
10
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:12
የግንብሽንም ጕልላት በቀይ ዕንቍ፥ በሮችሽንም በሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ዳርቻሽንም ሁሉ በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:12
Home
Bible
Plans
Videos