1
መጽሐፈ ኢያሱ 1:9
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ነውና ጽና፥ አይዞህ፥ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?
Compare
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 1:9
2
መጽሐፈ ኢያሱ 1:8
የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፥ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 1:8
3
መጽሐፈ ኢያሱ 1:7
ነገር ግን ጽና፥ እጅግ በርታ፥ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፥ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 1:7
4
መጽሐፈ ኢያሱ 1:5
በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፥ ከሙሴ ጋር እንደሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ አልጥልህም፥ አልተውህም።
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 1:5
5
መጽሐፈ ኢያሱ 1:6
ለአባቶቻቸው፦ እሰጣችኋለሁ ብዬ የማልሁላቸውን ምድር ለዚህ ሕዝብ ታወርሳለህና ጽና፥ አይዞህ።
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 1:6
6
መጽሐፈ ኢያሱ 1:3
ለሙሴ እንደ ነገርሁት የእግራችሁ ጫማ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ።
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 1:3
7
መጽሐፈ ኢያሱ 1:2
ባሪያዬ ሙሴ ሞቶአል፥ አሁንም አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ።
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 1:2
8
መጽሐፈ ኢያሱ 1:1
እንዲህም ሆነ፥ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 1:1
9
መጽሐፈ ኢያሱ 1:4
ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ የኬጥያውያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስክ ታላቁ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል።
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 1:4
10
መጽሐፈ ኢያሱ 1:18
በትእዛዝህ የሚያምፅ ሁሉ የምታዝዘውንም ቃል ሁሉ የማይሰማ፥ እርሱ ይገደል፥ ብቻ ጽና፥ አይዞህ።
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 1:18
11
መጽሐፈ ኢያሱ 1:10-11
ኢያሱም የሕዝቡን አለቆች፦ በሰፈሩ መካከል እለፉ፥ ሕዝቡንም፦ አምላካችሁ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ምድር እስከ ሦስት ቀን ይህን ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ልትወርሱአት ትገቡባታላችሁና ስንቃችሁን አዘጋጁ ብላችሁ እዘዙአቸው ብሎ አዘዘ።
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 1:10-11
Home
Bible
Plans
Videos