ኢሳይያስ 23
23
ስለ ጢሮስ የተነገረ ትንቢት
1ስለ ጢሮስ የተነገረ ንግር፤
የተርሴስ መርከቦች ሆይ፤ ዋይ በሉ!
ጢሮስ ተደምስሳለችና፣
ያለ ቤትና ያለ ወደብ ቀርታለች።
ከቆጵሮስ ምድር፣
ዜናው ወጥቶላቸዋል።
2እናንተ የባሕር ተጓዦች ያበለጠጓችሁ፣
በደሴቲቱ የምትኖሩ፣
የሲዶና ነጋዴዎችም ጸጥ በሉ።
3በታላላቅ ውሆች ላይ፣
ለጢሮስ የሺሖር እህል ይመጣላት ነበር፤
የአባይ መከር#23፥2-3 የማሶሬቱ ቅጅ ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ አንድ የሙት ባሕር ቅጅ ግን፣ ሲዶን በባሕሩ ላይ የምትሻገሪ፣ ተጓዦችሽ 3 የሺሖር እህል የአባይ መከር ይላል። ገቢዋ ነበር፤
እርሷም የመንግሥታቱ የንግድ መናኸሪያ ሆነች።
4አንቺ ሲዶና ሆይ፤
አንቺ የባሕር ምሽግ ሆይ፤ ዕፈሪ፤
ባሕሩ፣ “አላማጥሁም፤ አልወለድሁም፤
ወንዶችና ሴቶች ልጆችን አላሳደግሁም” ብሏልና።
5ከጢሮስ የሚመጣው ዜና፣
በግብጽ በሚሰማበት ጊዜ ጭንቅ ይይዛቸዋል።
6እናንተ በደሴቲቱ የምትኖሩ፣ በዋይታ አልቅሱ፤
ወደ ተርሴስም ተሻገሩ፤
7እግሮቿ ሩቅ አገር የወሰዷት፣
በዚያም እንድትሰፍር ያደረጓት፣
ጥንታዊቷ የድሮ ከተማ፣
የተድላ ከተማችሁ ይህች ናትን?
8አክሊል በምታቀዳጀዋ፣
ነጋዴዎቿ መሳፍንት በሆኑ፣
በምድር የከበሩ ሻጮችና ለዋጮች በነበሯት፣
በጢሮስ ላይ ይህን ያሰበ ማን ነበር?
9የክብርን ሁሉ ትዕቢት ሊያዋርድ፣
በምድር ከፍ ከፍ ያለውንም ሁሉ ዝቅ ሊያደርግ፣
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኗል።
10የተርሴስ ልጅ ሆይ፤
ከእንግዲህ የሚከለክልሽ የለምና
እንደ አባይ ወንዝ ምድርሽን አጥለቅልቂ።
11 እግዚአብሔር እጁን በባሕር ላይ ዘረጋ፤
መንግሥታቷንም አስደነገጠ፤
የከነዓንም#23፥11 አንዳንድ ቅጆች፣ ፊንቄ ይላሉ። ምሽጎች እንዲፈርሱ፣
ትእዛዝ ሰጠ፤
12እንዲህም አለ፤ “አንቺ የተቀጠቀጥሽ የሲዶን ድንግል ሆይ፤
ከእንግዲህ ደስ አይበልሽ!
“ተነሺ ወደ ቆጵሮስ ተሻገሪ፤
በዚያም እንኳ ሰላም አታገኚም።”
13እነሆ፤ የባቢሎናውያንን#23፥13 ወይም፣ ከለዳውያን ምድር ተመልከቱ፤
ሕዝቡ ከንቱ ሆኗል!
አሦራውያን የምድረ በዳ አራዊት
መፈንጪያ አደረጓት፤
የግንብ ማማቸውን ሠሩባት፤
ምሽጎቿን አወደሙ፤
የፍርስራሽ ክምር አደረጓት።
14እናንተ የተርሴስ መርከቦች፣ ዋይ በሉ፤
ምሽጋችሁ ፈርሷል!
15በዚያ ጊዜ ጢሮስ፣ የአንድ ንጉሥ የሕይወት ዘመን ያህል፣ ለሰባ ዓመታት ትረሳለች። ከሰባ ዓመት በኋላ ግን፣ ስለ ጋለሞታዪቱ የተዘፈነው በጢሮስ ላይ ይሆናል፤
16“አንች የተረሳሽ ጋለሞታ፤
በገና አንሺ፤ በከተማዪቱ ውስጥ ዙሪ፤
እንድትታወሺም፣
በገናሽን አሳምረሽ ምቺ፤ ብዙ ዘፈን ዝፈኚ።”
17ሰባው ዓመት ካለፈ በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይጐበኛታል፤ ወደ ቀድሞው የግልሙትና ሥራዋ ተመልሳ፣ በምድር ላይ ካሉት የዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋራ በንግዷ ትገለሙታለች። 18ያም ሆኖ ትርፏና ያገኘችው ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል፤ አይከማችም፤ አይጠራቀምም። ትርፏም በእግዚአብሔር ፊት ለሚኖሩት የተትረፈረፈ ምግብና ጥሩ ልብስ ይሆናል።
Currently Selected:
ኢሳይያስ 23: NASV
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.

: