ሮሜ 9
9
የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ምርጫ
1በክርስቶስ ሆኜ እውነት እናገራለሁ፤ አልዋሽም፤ ኅሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል። 2ታላቅ ሐዘንና የማያቋርጥ ጭንቀት በልቤ አለ። 3ለወገኖቼ ስል ስለ ወንድሞቼ እኔ ራሴ የተረገምሁና ከክርስቶስም ተለይቼ የተጣልሁ እንድሆን እንኳ እወድድ ነበር፤ 4እነርሱም የእስራኤል ሕዝብ ናቸው፤ ልጅ መሆን፣ መለኮታዊ ክብር፣ ኪዳን፣ ሕግን መቀበል፣ የቤተ መቅደስ ሥርዐትና ተስፋ የእነርሱ ናቸውና። 5አባቶችም የእነርሱ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የትውልድ ሐረጉ የሚቈጠረው ከእነርሱ ነው፤ እርሱም፣ ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘላለም የተመሰገነ አምላክ ነው!#9፥5 ወይም ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘላለም የተመሰገነ አምላክ ይሁን ወይም ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን አሜን።
6ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ተሽሯል ማለት አይደለም፤ ከእስራኤል የተወለደ ሁሉ እስራኤላዊ አይደለምና። 7ከአብርሃም ዘርም ስለ ሆኑ፣ ሁሉም ልጆቹ አይደሉም፤ ይልቁንስ፣ “ዘርህ በይሥሐቅ በኩል ይጠራልሃል”#9፥7 ዘፍ 21፥12 እንደ ተባለው ነው። 8ይህም ማለት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት የሥጋ ልጆች አይደሉም፤ ነገር ግን የአብርሃም ልጆች የተባሉት የተስፋው ልጆች ናቸው። 9“ጊዜው ሲደርስ እመለሳለሁ፤ ሣራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች”#9፥9 ዘፍ 18፥10 ተብሎ ተስፋው ተሰጥቷልና።
10ይህም ብቻ ሳይሆን፣ የርብቃ ልጆች አንድ አባት አላቸው፤ እርሱም አባታችን ይሥሐቅ ነው። 11መንትዮቹ ገና ሳይወለዱ፣ ወይም በጎም ሆነ ክፉ ሳያደርጉ፣ የእግዚአብሔር ሐሳብ በምርጫ ይጸና ዘንድ፣ 12በሥራ ሳይሆን ከጠሪው በመሆኑ፣ “ታላቁም ለታናሹ ይገዛል”#9፥12 ዘፍ 25፥23 ተብሎ ተነገራት። 13ይህም፣ “ያዕቆብን ወደድሁ፤ ዔሳውን ግን ጠላሁ”#9፥13 ሚል 1፥2 እና 3 ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።
14እንግዲህ ምን እንላለን? በእግዚአብሔር ዘንድ ዐመፃ አለን? ፈጽሞ! 15ለሙሴ፣
“የምምረውን እምረዋለሁ፤
የምራራለትንም ራራለታለሁ”#9፥15 ዘፀ 33፥19
ይላልና። 16እንግዲህ ይህ ከሰው ፍላጎት ወይም ጥረት ሳይሆን፣ ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው። 17መጽሐፍ ፈርዖንን፣ “ኀይሌ በአንተ እንዲታይ፣ ስሜም በምድር ሁሉ እንዲታወቅ ለዚህ አስነሣሁህ”#9፥17 ዘፀ 9፥16 ይላልና። 18ስለዚህ እግዚአብሔር ሊምረው ለሚወድደው ምሕረት ያደርግለታል፤ ልቡ እንዲደነድን የፈለገውንም ያደነድነዋል።
19ከእናንተ አንዱ፣ “ታዲያ እንደዚህ ከሆነ እግዚአብሔር እስከ አሁን ለምን ይወቅሠናል? ምክንያቱም ፈቃዱን ሊቋቋም የሚችል ማን አለ?” ይለኝ ይሆናል። 20ነገር ግን ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? “ሥራ ሠሪውን፣ ‘ለምን እንዲህ ሠራኸኝ?’ ይለዋልን?”#9፥20 ኢሳ 29፥16፤ 45፥9 21ሸክላ ሠሪ፣ ከሚሠራው ጭቃ፣ አንዳንዱን ሸክላ ለከበረ፣ ሌሎቹን ደግሞ ለተራ አገልግሎት የማድረግ መብት የለውምን?
22እግዚአብሔር ቍጣውን ለማሳየት፣ ኀይሉንም ለማሳወቅ ፈልጎ የቍጣው መግለጫ የሆኑትን፣ ለጥፋትም የተዘጋጁትን እጅግ ታግሦ ቢሆንሳ? 23አስቀድሞ ለክብር ላዘጋጃቸው፣ የምሕረቱም መግለጫዎች ለሆኑት፣ የክብሩ ባለጠግነት እንዲታወቅ ይህን አድርጎ እንደሆነስ? 24የጠራው ከአይሁድ ወገን ብቻ ሳይሆን ከአሕዛብ ወገን የሆንነውን እኛን እንኳ ሳይቀር አይደለምን? 25በሆሴዕ እንዲህ እንደሚል፤
“ሕዝቤ ያልሆኑትን፣ ‘ሕዝቤ’ ብዬ፣
ያልተወደደችውንም፣ ‘የተወደደች’ ብዬ እጠራለሁ።”#9፥25 ሆሴ 2፥23
26ደግሞም፣
“ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’
ተብሎ በተነገራቸው በዚያ ቦታ፣
‘የሕያው እግዚአብሔር ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።”#9፥26 ሆሴ 1፥10
27ኢሳይያስም ስለ እስራኤል እንዲህ ሲል ይጮኻል፤
“የእስራኤል ልጆች ቍጥር በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ቢሆንም፣
ትሩፉ ብቻ ይድናል።
28ጌታ ፍርዱን በምድር ላይ፣
በፍጥነትና ለመጨረሻ ጊዜ ይፈጽማልና።”#9፥28 ኢሳ 10፥22-23
29ይኸውም ቀደም ሲል ኢሳይያስ እንደ ተናገረው ነው፤
“የሰራዊት#9፥29 ግሪኩ ጸባኦት የሚለውን ዕብራይስጡን ቃል እንዳለ ወስዶታል። ጌታ፣
ዘር ባያስቀርልን ኖሮ፣
እንደ ሰዶም በሆንን፣
ገሞራንም በመሰልን ነበር።”#9፥29 ኢሳ 1፥9
የእስራኤል አለማመን
30እንግዲህ ምን እንበል? በእምነት የሆነውን ጽድቅ፣ ለጽድቅ ያልደከሙት አሕዛብ አገኙት፤ 31ነገር ግን የጽድቅን ሕግ የተከታተሉት እስራኤል አላገኙትም። 32ይህ ለምን ሆነ? በእምነት ሳይሆን በሥራ እንደ ሆነ አድርገው በመቍጠር ስለ ተከታተሉት ነው፤ እነርሱም፣ “በማሰናከያው ድንጋይ” ተሰናከሉ። 33ይህም፣
“እነሆ፤ የሚያደናቅፍ ድንጋይ፣
የሚጥልም ዐለት፣
በጽዮን አስቀምጣለሁ፤ በርሱም የሚያምን አያፍርም”#9፥33 ኢሳ 8፥14፤ 28፥16 ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
Currently Selected:
ሮሜ 9: NASV
Highlight
Share
Copy
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fen.png&w=128&q=75)
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.

: