1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14
14
በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ስጦታዎች
1እንግዲህ ፍቅርን ተከታተሉ፤ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ይልቁንም ትንቢት የመናገር ስጦታን በብርቱ ፈልጉ። 2በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገር ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ ምሥጢር የሆነውን ነገር በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ስለሚናገር የሚናገረውን ቃል የሚያውቀው የለም። 3ትንቢትን የሚናገር ግን ሌላውን ለማነጽ፥ ለማበረታታትና ለማጽናናት ለሰዎች ይናገራል። 4በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገር ሰው ራሱን ብቻ ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበረ ክርስቲያንን ያንጻል።
5ሁላችሁም በተለያዩ ቋንቋዎች ብትናገሩ እወድ ነበር፤ ይበልጥ የምወደው ግን ትንቢትን ብትናገሩ ነው፤ ማኅበረ ምእመናን እንዲታነጽ በተለያዩ ቋንቋዎች የተነገረውን የሚተረጒም ከሌለ፥ በተለያዩ ቋንቋዎች ከሚናገር ሰው ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ሰው ይበልጣል። 6እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ በተለያዩ ቋንቋዎች እየተናገርኩ ብመጣ ምን እጠቅማችኋለሁ? ይልቅስ የምጠቅማችሁ የእግዚአብሔርን ምሥጢር መግለጥን፥ ዕውቀትን፥ ትንቢት መናገርን፥ ትምህርትን ይዤላችሁ ብመጣ ነው።
7እንደ ዋሽንትና እንደ ክራር ያሉት ነፍስ የሌላቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች እንኳ የተለየ የድምፅ ቅኝት ከሌላቸው የሚሰጡት የሙዚቃ ድምፅ ምን መሆኑ እንዴት ይታወቃል? 8እምቢልታ በማይታወቅ ድምፅ ቢነፋ፤ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል? 9እንዲሁም እናንተ በቋንቋ ስትነጋገሩ ግልጥ በሆኑ ቃሎች ካልተናገራችሁ የምትናገሩትን ማን ሊያውቀው ይችላል? ለነፋስ እንደምትናገሩ ትሆናላችሁ። 10በዓለም ላይ ብዙ ቋንቋዎች አሉ፤ ትርጒም የሌለው ቋንቋም የለም። 11እንግዲህ እኔ የሚነገረውን ቋንቋ ትርጒም የማላውቅ ብሆን ለተናጋሪው ሰው እንግዳ እሆናለሁ፤ እርሱም ለእኔ እንግዳ ይሆናል። 12እናንተም የመንፈስ ቅዱስን ስጦታዎች በብርቱ ስለምትሹ በይበልጥ መፈለግ የሚገባችሁ ክርስቲያኖች የሚታነጹባቸው ስጦታዎች እንዲበዙላችሁ ነው።
13ስለዚህ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገር ሰው የመተርጐም ችሎታ እንዲኖረው ይጸልይ። 14በተለያዩ ቋንቋዎች ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል እንጂ አእምሮዬ ፍሬአልባ ነው። 15ታዲያ፥ ምን ማድረግ ይገባኛል? በመንፈሴ እጸልያለሁ፤ በአእምሮዬም ደግሞ እጸልያለሁ፤ በመንፈሴ እዘምራለሁ፤ በአእምሮዬም ደግሞ እዘምራለሁ። 16እንዲህማ ካልሆነ አንተ በመንፈስ እግዚአብሔርን ስታመሰግን፥ አንተ የምትለውን የማያውቅ እንግዳ ሰው ለምስጋና ጸሎትህ “አሜን” ሊል እንዴት ይችላል? 17እርግጥ አንተ ያቀረብከው የምስጋና ጸሎት በጥሩ ሁኔታ ነው፤ ነገር ግን ሌላው ሰው አይታነጽበትም።
18እኔ ከሁላችሁ ይበልጥ በተለያዩ ቋንቋዎች ስለምናገር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። 19ነገር ግን በተለያዩ ቋንቋዎች በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ ቃሎችን ከምናገር ይልቅ ሌሎችን ለማስተማር ስል በቤተ ክርስቲያን አምስት ቃላትን በሚታወቅ ቋንቋ በአእምሮዬ መናገር እወዳለሁ።
20ወንድሞቼ ሆይ! ለክፉ ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአስተሳሰባችሁስ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤ ይልቁንም በአስተሳሰባችሁ የበሰላችሁ ሁኑ። 21ይህም፦
“ ‘በተለያዩ ቋንቋዎች በሚናገሩ ሰዎችና
በባዕድ ሰዎች አፍ ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤
ይህም ሆኖ አይሰሙኝም’ ይላል ጌታ እግዚአብሔር”
ተብሎ በሕግ ተጽፎአል። #ኢሳ. 28፥11-12።
22ስለዚህ በተለያዩ ቋንቋዎች መናገር ምልክት የሚሆነው ለማያምኑ ሰዎች ነው እንጂ ለሚያምኑ ሰዎች አይደለም፤ የትንቢት ቃል መናገር ግን ምልክት የሚሆነው ለሚያምኑት ሰዎች እንጂ ለማያምኑ ሰዎች አይደለም።
23ክርስቲያኖች በሚሰበሰቡበት ጊዜ እያንዳንዱ ክርስቲያን በተለያዩ ቋንቋዎች ቢናገርና የማያውቁ ወይም የማያምኑ ሰዎች ቢመጡ ተናጋሪዎችን “እነዚህ ሰዎች አብደዋል” አይሉምን? 24ነገር ግን እያንዳንዱ የትንቢት ቃል ቢናገርና የማያምን ወይም የማያውቅ ሰው ቢመጣ በሚሰማው ቃል ሁሉ ይወቀሳል፤ እንዲሁም በሚሰማው ቃል ሁሉ ይፈረድበታል። 25በልቡ የተሰወረው ነገር ይገለጣል፤ በግንባሩም ተደፍቶ “በእርግጥ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ነው!” በማለት ለእግዚአብሔር ይሰግዳል።
በማኅበር ጸሎት ጊዜ ሊኖር የሚገባው ሥነ ሥርዓት
26ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ምን ማድረግ ይገባል? ለጸሎት በምትሰበሰቡበት ጊዜ ከእናንተ አንዱ የመዘመር ስጦታ አለው፤ ሌላው የማስተማር ስጦታ አለው፤ አንዱ ስውር የሆነውን ነገር የመግለጥ ስጦታ አለው፤ አንዱ በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ስጦታ አለው፤ ሌላው የመተርጐም ስጦታ አለው። ታዲያ፥ ይህ ሁሉ ስጦታ ክርስቲያኖችን የሚያንጽ መሆን አለበት። 27በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ቢኖሩ ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት ሆነው በየተራ ይናገሩ፤ እነርሱ የሚናገሩትንም ሌላ ሰው ይተርጒም። 28የሚተረጒም ሰው ከሌለ ግን በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩት በስብሰባ ላይ ዝም ይበሉ፤ ለራሳቸውና ለእግዚአብሔር ብቻ ይናገሩ። 29ትንቢት የሚናገሩ ሁለት ወይም ሦስት ሆነው ይናገሩ፤ ሌሎቹ ግን የተነገረውን አዳምጠው በጥንቃቄ ያመዛዝኑ። 30በስብሰባ ላይ ለሚገኝ ሌላ ሰው አንዳች ራእይ ቢገለጥለት፤ የመጀመሪያው ተናጋሪ ዝም ይበል። 31እያንዳንዱ እንዲማርና እንዲጽናና ሁላችሁም በየተራ የእግዚአብሔርን መልእክት መናገር ትችላላችሁ። 32የነቢያት የትንቢት መንፈስ ለነቢያት ይታዘዛል። 33በእግዚአብሔር ሕዝብ አብያተ ክርስቲያን ሁሉ ዘንድ እንደሚደረገው እግዚአብሔር የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለም። 34ሴቶች በጸሎት ስብሰባ ጊዜ ዝም ይበሉ፤ ሕግ እንደሚያዘው እንዲታዘዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውም። 35አንዳንድ ነገርን ማወቅ ቢፈልጉ ባሎቻቸውን በቤታቸው ይጠይቁ፤ በጸሎት ስብሰባ ጊዜ ሴት እንድትናገር ተገቢ አይደለም።
36ለመሆኑ የእግዚአብሔር ቃል የመጣው ከእናንተ ነው? ወይስ የእግዚአብሔር ቃል የደረሰው ወደ እናንተ ብቻ ነው? 37እኔ ነቢይ ነኝ ወይም እኔ መንፈሳዊ ስጦታ አለኝ የሚል ሰው ቢኖር ይህ የጻፍኩላችሁ የጌታ ትእዛዝ መሆኑን ይወቅ። 38ይህን የማያውቅ ቢኖር እርሱም አይታወቅም።
39ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፤ በተለያዩ ቋንቋዎች መናገርንም አትከልክሉ። 40ነገር ግን ሁሉ ነገር በአግባብና በሥነ ሥርዓት ይሁን።
Currently Selected:
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: