አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 3
3
የእግዚአብሔር ለሳሙኤል መገለጥ
1ወጣቱ ሳሙኤል በዔሊ የአመራር ሥልጣን ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ዘወትር አይሰማም ነበር፤ ራእይም አይታይም ነበር። 2በእርጅና ምክንያት ዐይኖቹ ፈዘው የነበሩት ዔሊ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ሌሊት በመኝታ ክፍሉ ተኝቶ ነበር። 3ገና የቤተ መቅደሱ መብራት ሳይጠፋ ሳሙኤል የተቀደሰው የቃል ኪዳን ታቦት ባለበት መቅደስ ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ 4እግዚአብሔር ሳሙኤልን ጠራው፤ ሳሙኤልም “እነሆ አለሁ ጌታዬ” አለ። 5ወደ ዔሊ ዘንድ ሮጦ በመሄድ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለ።
ዔሊ ግን “እኔ አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ሂድና ተኛ” አለው፤ ሳሙኤልም ተመልሶ ተኛ።
6እግዚአብሔር እንደገና ሳሙኤልን ጠራው፤ ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ “እነሆ! ስለ ጠራኸኝ መጥቼአለሁ” አለው፤ ዔሊ ግን “ልጄ ሆይ! እኔ አልጠራሁህም፤ ወደ መኝታህ ተመልሰህ ተኛ” አለው።
7ሳሙኤልም ከዚያ በፊት እግዚአብሔር ተናግሮት ስለማያውቅ የእግዚአብሔር ድምፅ መሆኑን አላወቀም ነበር።
8እግዚአብሔርም እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ሳሙኤልን ጠራው፤ ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ “እነሆ! ስለጠራኸኝ መጥቻለሁ” አለው።
ከዚህም በኋላ ሳሙኤልን ይጠራው የነበረው እግዚአብሔር መሆኑን ዔሊ ተገነዘበ፤ 9ስለዚህም “ወደ መኝታህ ተመልሰህ ሂድ፤ እንደገናም የጠራህ እንደ ሆነ ‘ጌታ ሆይ፥ እነሆ እኔ አገልጋይህ እሰማለሁና ተናገር’ በለው” ሲል ሳሙኤልን መከረው። ሳሙኤልም ተመልሶ ወደ መኝታው ሄደ።
10እግዚአብሔርም መጥቶ በዚያ ቆመ፤ ከዚያም በፊት ያደርግ በነበረው ዐይነት “ሳሙኤል! ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው።
ሳሙኤልም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ እሰማለሁና ተናገር” አለው።
11እግዚአብሔር እንዲህ አለው፦ “እነሆ እኔ በእስራኤል ላይ አንድ ነገር የማደርግበት ቀን ተቃርቦአል፤ ያን ነገር በጆሮው የሚሰማው ሁሉ ይዘገንነዋል። 12በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ አስቀድሜ የተናገርኩትን ብርቱ የማስጠንቀቂያ ቃል ሁሉ በተግባር እፈጽማለሁ፤ 13ልጆቹ በእኔ ላይ የንቀት ተግባር ሲፈጽሙ እርሱ ስላልገሠጻቸው ቤተሰቡን ለዘለዓለም እቀጣለሁ ብዬ ነግሬዋለሁ። 14ስለዚህ የዔሊ ቤተሰብ ኃጢአት በመሥዋዕትም ሆነ በቊርባን ለዘለዓለም አይሰረይም ብዬ በመሐላ ተናግሬአለሁ።”
15ሳሙኤልም እስኪነጋ ድረስ ተኝቶ ቈየ፤ በነጋም ጊዜ ተነሥቶ የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ከፈተ፤ ያየውንም ራእይ ለዔሊ ለመንገር ፈራ፤ 16ዔሊ ግን ሳሙኤልን “ልጄ ሳሙኤል ሆይ!” ሲል ጠራው።
ሳሙኤልም “እነሆ አለሁ ጌታዬ!” ሲል መለሰ።
17ዔሊም “እግዚአብሔር የነገረህ ቃል ምንድን ነው? ከእኔ ምንም ነገር አትደብቅ፤ አንዳች ነገር ብትደብቅ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ብርቱ ቅጣት ያምጣብህ” አለው። 18ከዚህም በኋላ ሳሙኤል ሁሉንም ነገር ለዔሊ አስረዳው፤ ሰውሮ ያስቀረው ምንም ነገር አልነበረም፤ ዔሊም “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህም መልካም መስሎ የታየውን ነገር ያድርግ” አለ።
19ሳሙኤል እያደገ ሄደ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበር ሳሙኤል የሚናገረውን ቃል ሁሉ ይፈጽምለት ነበር፤ 20ከዚህም የተነሣ በሀገሪቱ ዳር እስከ ዳር የሚኖሩ እስራኤላውያን ሁሉ ሳሙኤል የእግዚአብሔር ነቢይ መሆኑን ዐወቁ፤ 21እግዚአብሔርም በሴሎ መገለጡን ቀጠለ፤ እዚያም በቃሉ ለሳሙኤል ተገለጠለት። የሳሙኤልም ቃል በመላው እስራኤል ተደማጭነትን አገኘ።
Currently Selected:
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 3: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: