1 ተሰሎንቄ ሰዎች 3
3
1ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ መታገሥ ባለመቻላችን በአቴና ብቻችንን መቅረት መልካም ሆኖ ታየን። #ሐ.ሥ. 17፥15። 2ወንድማችንንና የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን፥ የክርስቶስን መልካም ዜና በማብሠር የሥራ ጓደኛችንን ጢሞቴዎስን ልከንላችኋል፤ የላክንላችሁም እንዲያጸናችሁና በእምነት እንድትበረቱ እንዲመክራችሁ ነው፤ 3ይህም በደረሰባችሁ መከራ እንዳትናወጡ ያደርጋችኋል፤ ይህ መከራ ለእኛ የተወሰነልን ዕጣ መሆኑን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። 4እንዲያውም ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ መከራ እንደሚደርስብን አስቀድመን እንነግራችሁ ነበር፤ እንደምታውቁትም መከራው ደርሶብናል፤ 5በዚህ ምክንያት ከእንግዲህ ወዲህ በትዕግሥት መጠበቅ ባለመቻሌ ስለ እምነታችሁ ማወቅ ፈልጌ ጢሞቴዎስን ወደ እናንተ ላክሁት፤ እርሱን የላክሁትም ምናልባት ፈታኙ በአንድ መንገድ ፈትኖአችሁ ይሆናል፤ ሥራችንም ከንቱ ሆኖ ቀርቶአል በማለት ፈርቼ ነው።
6አሁን ግን ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ወደ እኛ መጥቶ ስለ እምነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ ደስ የሚያሰኝ ዜና ነገረን፤ እንዲሁም እናንተ ዘወትር በመልካም እንደምታስታውሱንና እኛ እናንተን ለማየት የምንናፍቃችሁን ያኽል እናንተም እኛን ለማየት እንደምትናፍቁ ነገረን። #ሐ.ሥ. 18፥5። 7ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፥ እኛ የምንገኘው በችግርና በመከራ ውስጥ ቢሆንም እንኳ በእምነታችሁ ምክንያት በእናንተ ተጽናንተናል። 8የእናንተ በጌታ ኢየሱስ ጸንቶ መኖር ለእኛ ሕይወታችን ነው። 9እነሆ፥ አሁን ስለ እናንተ ምስጋና እናቀርባለን፤ በእናንተም ምክንያት በእርሱ ፊት ስላለን ደስታ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። 10ሌሊትና ቀን በብርቱ የምንጸልየው በዐይነ ሥጋ እንድናያችሁና በእምነታችሁ የጐደለውን ለመሙላት እንድንችል ነው።
11አሁንም አምላካችንና አባታችን ራሱ ጌታችን ኢየሱስም ወደ እናንተ እንድንመጣ መንገዳችንን ያቅናልን። 12እኛ እንደምናፈቅራችሁ ጌታ እርስ በርስና ለሌሎችም ሁሉ ያላችሁ ፍቅር እንዲያድግና እንዲበዛ ያድርግላችሁ፤ 13በዚህ ዐይነት ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በሚመጣበት ጊዜ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁ ነቀፋ የሌለበትና ቅዱስ እንዲሆን ያበረታችኋል።
Currently Selected:
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 3: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: