1 ተሰሎንቄ ሰዎች መግቢያ
መግቢያ
ተሰሎንቄ መቄዶንያ የተባለው የሮም ግዛት ዋና ከተማ ነበረች፤ ጳውሎስ በተሰሎንቄ ቤተ ክርስቲያን ያቋቋመው ፊልጵስዩስን ትቶ ከሄደ በኋላ ነው፤ ይሁን እንጂ የአይሁድን ሃይማኖት ሊቀበሉ ተቃርበው የነበሩት አሕዛብ ጳውሎስ በሚያቀርበው የክርስትና መልእክት ተስበው ስለ ነበር አይሁድ ቀንተው በጳውሎስ ላይ ተቃውሞ አስነሥተው ነበር፤ ስለዚህም ጳውሎስ ተሰሎንቄን ለቆ ወደ ቤርያ ለመሄድ ተገደደ፤ ዘግየት ብሎም ወደ ቆሮንቶስ እንደ ደረሰ የቅርብ ረዳቱ የነበረው ጢሞቴዎስ ወደ ተሰሎንቄ ሄዶ እንደ ተመለሰ በቤተ ክርስቲያን ስላለው ሁኔታ በዝርዝር አስረዳው።
ጳውሎስ የመጀመሪያውን መልእክት ለተሰሎንቄ ሰዎች የጻፈው ክርስቲያኖችን ለማበረታታትና ለማጽናናት ነበር፤ ስለ እምነታቸውና ስለ ፍቅራቸው መልካም ወሬ በመስማቱ እግዚአብሔርን ያመሰግናል፤ ጳውሎስም በመካከላቸው በተገኘበት ጊዜ ምን ዐይነት ሕይወት እንደ ኖረ ያስታውሳቸዋል፤ ከዚያም የክርስቶስን ዳግም ምጽአት አስመልክቶ ስለ ተነሡት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፤ ከእነዚህም ጥያቄዎች ጥቂቶቹ፦
“ክርስቶስ ከመመለሱ በፊት የሞተ አማኝ የክርስቶስ መመለስ በሚያስገኘው የዘለዓለም ሕይወት ተካፋይ ይሆናልን? ክርስቶስ ተመልሶ የሚመጣው መቼ ነው?” የሚሉት ናቸው፤ ጳውሎስም ይህን አጋጣሚ በመጠቀም “የክርስቶስን ዳግም ምጽአት ትምህርት በተስፋ እየተጠባበቃችሁ እስከዚያ ድረስ በጸጥታ ሥራችሁን ሥሩ” በማለት ይመክራቸዋል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1
የጳውሎስ ደስታና ምስጋና 1፥2—3፥13
የክርስቲያን ሕይወት መመሪያ 4፥1-12
ስለ ክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት ትምህርት 4፥13—5፥11
የመጨረሻ ምክር 5፥12-22
ማጠቃለያ 5፥23-28
Currently Selected:
1 ተሰሎንቄ ሰዎች መግቢያ: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: