1 ወደ ጢሞቴዎስ መግቢያ
መግቢያ
ጢሞቴዎስ የተባለው ወጣት ክርስቲያን ትውልዱ ከታናሽቱ እስያ ሲሆን፥ በእናቱ አይሁዳዊ፥ በአባቱ ደግሞ ግሪካዊ ነበር፤ የጳውሎስ የሥራ ጓደኛና በወንጌል ተልእኮውም የቅርብ ረዳቱ ነበር፤ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የጻፈለት የመጀመሪያው መልእክት፥ በሦስት ዋና ዋና ነገሮች ላይ ያተኰረ ነው።
ከሁሉ በማስቀደም መልእክቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተነሥቶ ስለ ነበረው የሐሰት ትምህርት የሚያስጠነቅቅ ነበር፤ ይህም ዕንግዳ ትምህርት በከፊል የአይሁድ፥ በከፊል ደግሞ የሌሎች ሕዝቦችን ሐሳብ የያዘ ሲሆን፥ “የሚታየው ዓለም በኃጢአት የተበከለ ስለ ሆነ መዳን ሊገኝ የሚችለው ልዩ በሆነ ምሥጢራዊ ዕውቀትና ከአንዳንድ ምግቦችና ከጋብቻ በመጠበቅ ነው” በሚል ሐሳብ ላይ የተመሠረተ ነበር። በተጨማሪም መልእክቱ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና የአምልኮ ሥርዓት ትምህርታዊ መመሪያ፥ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና ረዳቶቻቸው ሊኖራቸው ስለሚገባ ጠባይ መግለጫ የያዘ ነው። በመጨረሻም ጢሞቴዎስ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ እንዴት ሊሆን እንደሚገባውና በተለያዩ ማኅበረ ምእመናን ዘንድ ስላለው ኀላፊነት ጳውሎስ የሰጠውን ምክር እናገኛለን።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1-2
ስለ ቤተ ክርስቲያንና አገልጋዮችዋ 1፥3—3፥16
ለጢሞቴዎስ ስለ አገልግሎቱ የተሰጠ ትምህርት 4፥1—6፥21
Currently Selected:
1 ወደ ጢሞቴዎስ መግቢያ: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: