2 የጴጥሮስ መልእክት 1:3-4
2 የጴጥሮስ መልእክት 1:3-4 አማ05
በክብሩና በደግነቱ የጠራንን እርሱን በማወቃችን መለኮታዊ ኀይሉ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለማምለክ የሚያስፈልገንን ሁሉ ሰጥቶናል። በክብሩና በቸርነቱ ክቡር ዋጋ ያለውንና እጅግ ታላቅ የሆነውን ተስፋውን አግኝተናል፤ በእነዚህም አማካይነት እናንተ በክፉ ምኞት ምክንያት በዚህ ዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች ሆናችኋል።