2 ወደ ጢሞቴዎስ መግቢያ
መግቢያ
ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የጻፈው ይህ ሁለተኛው መልእክት፥ ጳውሎስ የቅርብ ረዳቱና የሥራ ጓደኛው ለሆነው ለወጣቱ ጢሞቴዎስ የሰጠውን ምክር የያዘ ነው፤ በበለጠም የመከረው በትዕግሥት እንዲጸና ነው፤ ጢሞቴዎስ የምክርና የማበረታቻ ቃል ያገኘው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በታማኝነት እንዲመሰክር፥ የምሥራቹን ቃልና የብሉይ ኪዳንን ትምህርት አጥብቆ እንዲይዝና ምንም እንኳ መከራና ተቃውሞ ቢበዛበትም፥ በማስተማርና በወንጌል ሰባኪነት ሥራው እንዲተጋ ነበር።
ጢሞቴዎስ በተለይ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው በሞኝነት ከሚደረገው ከከንቱ ክርክር እንዲርቅ ነበር፤ እንዲህ ዐይነቱ ነገር የሚሰሙትን ከማጥፋት በቀር ሌላ የሚሰጠው ጥቅም የለውም።
በዚህ ሁሉ ጢሞቴዎስ ማስታወስ የነበረበት የጳውሎስን ሕይወትና የኑሮ ዓላማ በተለይም እምነቱን፥ ትዕግሥቱን፥ ፍቅሩን፥ መጽናቱንና በስደት የደረሰበትን መከራ በምሳሌነት እንዲከተለው ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1-2
ለጢሞቴዎስ የተሰጠ ምክር 1፥3—2፥13
በክሕደት ጊዜ ታማኝ ሆኖ መገኘት 2፥14—4፥5
በወቅቱ ስለ ነበሩት ሁኔታዎችና አስፈላጊ መመሪያዎች 4፥6-18
ማጠቃለያ 4፥19-22
Currently Selected:
2 ወደ ጢሞቴዎስ መግቢያ: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: