የሐዋርያት ሥራ 26
26
ጳውሎስ በአግሪጳ ፊት ያደረገው ንግግር
1አግሪጳ ጳውሎስን “ስለ ራስህ እንድትናገር ተፈቅዶልሃል” አለው፤ ጳውሎስም እጁን ዘረጋና እንዲህ ሲል የመከላከያ መልሱን ሰጠ።
2“ንጉሥ አግሪጳ ሆይ! አይሁድ በከሰሱኝ ነገር ሁሉ ዛሬ በአንተ ፊት የመከላከያ መልስ ስሰጥ እጅግ ደስ ይለኛል። 3በተለየም አንተ የአይሁድን ሥርዓትና ክርክር ሁሉ ጠንቅቀህ ታውቃለህ፤ ስለዚህ በትዕግሥት እንድታዳምጠኝ እለምንሃለሁ።
4“ከልጅነቴ ጀምሮ እንዴት እንደ ኖርኩ አይሁድ ያውቃሉ፤ ከመጀመሪያ አንሥቶ በሕዝቤ መካከልና በኢየሩሳሌም የኖርኩትን ሕይወቴን ያውቁታል። 5ደግሞም ሊመሰክሩ ቢፈቅዱ ከሃይማኖታችን በጣም ወግ አጥባቂ ከሆነው ክፍል ፈሪሳዊ ሆኜ እንደ ኖርኩ ከመጀመሪያው አንሥቶ ያውቃሉ። #ሐ.ሥ. 23፥6፤ ፊል. 3፥5። 6አሁን ግን ለፍርድ እዚህ የቆምኩት እግዚአብሔር ለአባቶቻችን ስለ ሰጠው የቃል ኪዳን ተስፋ ነው። 7ወደዚህ ተስፋ ለመድረስ ዐሥራ ሁለቱ ነገዶቻችን እግዚአብሔርን ሌት ተቀን እያመለኩ ይጠባበቁ ነበር፤ ንጉሥ ሆይ! እኔም በአይሁድ የተከሰስኩበት በዚህ ተስፋ ምክንያት ነው። 8እግዚአብሔር ሙታንን የሚያስነሣ መሆኑ ስለምን በእናንተ ዘንድ ሊታመን የማይቻል ሆነ?
9“እኔ ራሴ የናዝሬቱን የኢየሱስን ስም የተቻለኝን ያኽል መቃወም አለብኝ ብዬ አስብ ነበር። #ሐ.ሥ. 8፥3፤ 22፥4-5። 10በኢየሩሳሌም ያደረግኹትም ይህንኑ ነበር፤ ከካህናት አለቆች በተቀበልኩት ሥልጣን ከምእመናን ብዙዎቹ ወደ ወህኒ ቤት እንዲገቡ አድርጌአለሁ፤ ሲገድሉአቸውም ከገዳዮቻቸው ጋር ተስማምቻለሁ። 11ብዙ ጊዜ በየምኲራቡ እንዲቀጡና በጌታ ላይ የስድብ ቃል እንዲናገሩ አስገድዳቸው ነበር፤ በእነርሱ ላይ በጣም ተቈጥቼም ወደ ሌሎች የውጪ አገር ከተሞች እንኳ ወጥቼ እየሄድኩ አሳድዳቸው ነበር።
ጳውሎስ ወደ ክርስቶስ እንዴት እንደ ተመለሰ መተረኩ
(ሐ.ሥ. 9፥1-19፤ 22፥6-16)
12“ለዚሁ ጉዳይ ከካህናት አለቆች ሙሉ ሥልጣንና ትእዛዝ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ እጓዝ ነበር፤ 13ንጉሥ ሆይ! በመንገድ ሳለሁ ልክ እኩለ ቀን ሲሆን ከፀሐይ ብርሃን የሚበልጥ ብርሃን አየሁ፤ ይህም ብርሃን በእኔና ከእኔ ጋር በሚጓዙት ሰዎች ዙሪያ ከሰማይ አበራ። 14ሁላችንም በመሬት ላይ ወድቀን ሳለ በአይሁድ ቋንቋ ‘ሳውል! ሳውል! ስለምን ታሳድደኛለህ? በሰይፍ ስለት ላይ ብትቆም ራስህን ትጐዳለህ’ የሚል ድምፅ ሰማሁ። 15እኔም ‘ጌታ ሆይ! አንተ ማን ነህ?’ አልኩ፤ ጌታም እንዲህ አለኝ፦ ‘እኔ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ። 16አሁን ግን ተነሥና በእግርህ ቁም፤ እኔ የተገለጥኩልህ አሁን እኔን ባየህበትና ወደፊትም እኔ ለአንተ በምገለጥበት ነገር አገልጋይና ምስክር እንድትሆነኝ ልሾምህ ፈልጌ ነው። 17ከእስራኤል ሕዝብና ወደ እነርሱ ከምልክህ አሕዛብ እጅ አድንሃለሁ። 18ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድታወጣቸው ከሰይጣንም ግዛት ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በእኔ በማመናቸው ምክንያት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ፤ በተመረጡት መካከልም ርስትን ይካፈላሉ።’
ጳውሎስ ስለ ሥራው ሁኔታ ማስረዳቱ
19“ስለዚህ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ! ከሰማይ ለተሰጠኝ ራእይ እምቢተኛ አልሆንኩም። 20ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ያሉት ሰዎች፥ ቀጥሎም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምድር ሁሉ ያሉት እንዲሁም አሕዛብ ጭምር ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ አስተማርኳቸው፤ ንስሓ መግባታቸውን የሚያመለክት ነገር እንዲያደርጉም አስተማርኳቸው። #ሐ.ሥ. 9፥20፤28-29። 21በዚህ ምክንያት አይሁድ በቤተ መቅደስ እንዳለሁ ያዙኝና ሊገድሉኝ ሞከሩ። 22እስከ ዛሬ ድረስ የእግዚአብሔር ርዳታ አልተለየኝም፤ ስለዚህ ለትንሹም ለትልቁም እየመሰከርኩ እዚህ ቆሜአለሁ፤ ነቢያትና ሙሴ አስቀድመው እንዲህ ይሆናል ያሉትን ከመናገር በቀር ሌላ ምንም አልተናገርኩም። 23እነርሱም የተናገሩት ‘መሲሕ መከራ ይቀበላል፤ ከሞት በመነሣትም የመጀመሪያ ሆኖ የመዳንን ብርሃን ለእስራኤል ሕዝብና ለአሕዛብ ይገልጣል’ ብለው ነው።” #ኢሳ. 42፥6፤ 49፥6፤ 1ቆሮ. 15፥20።
24ጳውሎስ ይህን ሲናገር ሳለ ፊስጦስ “ጳውሎስ ሆይ! አሁንስ አበድክ፤ ብዙ መማርህ ወደ እብደት አድርሶሃል!” ሲል ጮኾ ተናገረ።
25ጳውሎስ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እጅግ የተከበርክ ፊስጦስ ሆይ! እውነተኛውንና ትክክለኛውን ነገር እናገራለሁ እንጂ አላበድኩም። 26በፊቱ በግልጥ የተናገርኩት ንጉሥ ይህን ነገር ያውቃል። ይህም በስውር ያልተደረገ ስለ ሆነ ንጉሡ እንደሚረዳው እርግጠኛ ነኝ። 27ንጉሥ አግሪጳ ሆይ! ነቢያትን ታምን የለምን? እንደምታምን ዐውቃለሁ።”
28አግሪጳም ጳውሎስን፥ “አንተ በዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ክርስቲያን ልታደርገኝ ነው እኮ” አለው። 29ጳውሎስም “በአጭር ጊዜም ይሁን በረጅም ጊዜ አንተ ብቻ ሳትሆን ዛሬ ንግግሬን የሰሙ ሁሉ ከዚህ ከእስራቴ በቀር እንደ እኔ እንዲሆኑ እግዚአብሔርን እለምናለሁ!” አለ።
30ከዚህ በኋላ ንጉሡ፥ ገዢውና በርኒቄ፥ ከእነርሱ ጋር ተቀምጠው የነበሩትም ሰዎች ሁሉ ተነሡ። 31ከዚያም ወጥተው ሲሄዱ፥ “ይህ ሰው ለሞት ወይም ለእስራት የሚያበቃው ምንም ነገር አላደረገም” ተባባሉ። 32አግሪጳም ፊስጦስን “ይህ ሰው ወደ ሮሙ ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ ባይል ኖሮ በነጻ በተለቀቀ ነበር” አለ።
Currently Selected:
የሐዋርያት ሥራ 26: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: