ኦሪት ዘዳግም 5
5
ዐሥሩ ትእዛዞች
(ዘፀ. 20፥1-17)
1ሙሴም የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ ዛሬ የምነግራችሁን ሕግና ሥርዓት ሁሉ አድምጡ፤ በጥንቃቄም አጥንታችሁ እነዚህን ትእዛዞች ጠብቁ። 2እግዚአብሔር አምላካችን በሲና ተራራ ላይ ቃል ኪዳን አደረገ፤ 3ቃል ኪዳን ያደረገውም ከአባቶቻችን ጋር ብቻ ሳይሆን፥ አሁን በሕይወት ካለነውም ከእኛ ሁሉ ጋር ነው። 4እዚያም በተራራው ላይ በተቀጣጠለው እሳት ውስጥ ሆኖ ፊት ለፊት አነጋገራችሁ፤ 5እናንተ እሳቱን በመፍራት ወደ ተራራው መውጣት ስለ ፈራችሁ እኔ በዚያን ጊዜ እርሱ የሚለውን ሁሉ ልነግራችሁ በእናንተና በእግዚአብሔር መካከል ቆምኩ፤
“እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ 6‘በባርነት ተገዢ ሆነህ ከኖርክበት ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤
7“ ‘ከእኔ በቀር ሌሎችን አማልክት አታምልክ።
8“ ‘በሰማይ፥ ወይም በምድር፥ ወይም ከምድር በታች በውሃ ውስጥ ከሚገኙት ነገሮች የተቀረጹ ምስሎች ሠርተህ አታምልካቸው፤ 9እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፥ እኔን ትተው ሌሎች አማልክትን የሚያመልኩትን ሰዎች፥ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች፥ እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ የምበቀል ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆንኩ እነዚያን የተቀረጹ ምስሎች አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም። #ዘሌ. 26፥1፤ ዘዳ. 4፥15-18፤ 27፥15። 10ለሚወዱኝና ትእዛዞቼን ለሚጠብቁ ግን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ዘለዓለማዊ ፍቅሬን አሳያቸዋለሁ። #ዘፀ. 34፥6-7፤ ዘኍ. 14፥18፤ ዘዳ. 7፥9-10።
11“ ‘የእኔን የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ሰው እግዚአብሔር ሳይቀጣው አይቀርም። #ዘሌ. 19፥12።
12“ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዝኩህ የሰንበትን ቀን ጠብቅ፤ ቀድሰውም፤ #ዘፀ. 16፥23-30፤ 31፥12-14። 13ሥራህን ሁሉ በስድስት ቀኖች ሠርተህ ታከናውናለህ፤ 14ሰባተኛው ቀን ግን ለእኔ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ምንም ዐይነት ሥራ አትሥራ፤ አንተም ሆንክ ልጆችህ፥ አገልጋዮችህም ሆኑ እንስሶችህ በአገርህ ውስጥ የሚኖሩ መጻተኞችም ቢሆኑ ምንም ሥራ አትሥሩበት፤ አገልጋዮችህም ልክ እንደ አንተው ዕረፍት ያድርጉ። #ዘፀ. 23፥12፤ 31፥15፤ 34፥21፤ 35፥2፤ ዘሌ. 23፥3። 15በግብጽ ምድር ባሪያ የነበርክ መሆንህን አስታውስ፤ አምላክህ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይልና በብርቱ ሥልጣን ከዚያ አወጣህ፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ታከብር ዘንድ ያዘዘህ ስለዚህ ነው።
16“ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ባዘዝኩህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል። #ዘዳ. 27፥16፤ ማቴ. 15፥4፤ 19፥19፤ ማር. 7፥10፤ 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20፤ ኤፌ. 6፥2-3።
17“ ‘አትግደል፤ #ዘፍ. 9፥6፤ ዘሌ. 9፥6፤ ዘሌ. 24፥17፤ ማቴ. 5፥21፤ 19፥18፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20፤ ሮም 13፥9፤ ያዕ. 2፥11።
18“ ‘አታመንዝር፤ #ዘሌ. 20፥10፤ ማቴ. 5፥27፤ 19፥18፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥2።
19“ ‘አትስረቅ፤ #ዘሌ. 19፥11፤ ማቴ. 19፥18፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20፤ ሮም 13፥9።
20“ ‘በማንም ሰው ላይ በሐሰት አትመስክር፤ #ዘፀ. 23፥1፤ ማቴ. 19፥18፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20።
21“ ‘የሌላውን ሰው ሚስቱን፥ ቤቱን፥ ርስቱን፥ አገልጋዮቹን፥ ከብቱን፥ አህዮቹንም ሆነ ማናቸውንም ንብረቱን ሁሉ አትመኝ።’ #ሮም 7፥7፤ 13፥9።
22“በተሰበሰባችሁ ጊዜ እግዚአብሔር በተራራው ላይ ሆኖ ለእናንተ ለሁላችሁም የሰጣችሁ ትእዛዞች እነዚህ ናቸው፤ በእሳት፥ በደመናና በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ብርቱ በሆነ ታላቅ ድምፅ በተናገረ ጊዜ የሰጣችሁ ትእዛዞች እነዚህ ብቻ ናቸው። እነርሱንም በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጽፎ ለእኔ ሰጠኝ።
የሕዝቡ ፍርሀት
(ዘፀ. 20፥18-21)
23“ተራራው በእሳት ይነድ በነበረበት ወቅት ከጨለማው ውስጥ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ የነገድ አለቆችና መሪዎች ሁሉ ወደ እኔ መጥታችሁ፥ 24እንዲህ አላችሁ፦ ‘በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር በሰማነው ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችን ታላቅነቱንና ክብሩን በግልጥ አሳይቶናል፤ እግዚአብሔር ካነጋገረው በኋላ እንኳ ሰው በሕይወት መኖር እንደሚችል በዛሬው ዕለት አይተናል። 25ነገር ግን ያ ብርቱ እሳት ያጠፋናል፤ ታዲያ ለምን መሞት እንፈልጋለን? እግዚአብሔር አምላካችን እንደገና ቢናገረን እንሞታለን። 26ሕያው እግዚአብሔር በእሳት ውስጥ ሆኖ ከተናገረው በኋላ በሕይወት የኖረ ከሰው ዘር መካከል አንድ ሰው እንኳ ይገኛልን? 27ስለዚህ ወደ እርሱ ቀርበህ እግዚአብሔር አምላካችን የሚለውን ሁሉ አዳምጥ፤ ተመልሰህም እርሱ ያለውን ሁሉ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እንታዘዛለን።’ #ዕብ. 12፥18-19።
28“እግዚአብሔርም፥ ይህን ስትሉኝ በሰማ ጊዜ እንዲህ አለኝ፤ ‘እነዚህ ሰዎች ለአንተ የተናገሩትን ሁሉ ሰምቻለሁ፤ አባባላቸውም ትክክል ነው፤ 29ሁልጊዜ በዚህ ዐይነት ቢያስቡማ እንዴት መልካም ነበር! ሁልጊዜ ቢያከብሩኝና ትእዛዞቼንም ሁሉ ቢፈጽሙ ሁሉ ነገር ለእነርሱና ለዘሮቻቸው ለዘለዓለም በመልካም ሁኔታ በተከናወነላቸው ነበር። 30አሁንም ሂድና ወደየድንኳናቸው እንዲመለሱ ንገራቸው። 31አንተ ግን እዚህ እኔ አጠገብ ቁም፤ እኔም ሕግጋቴን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቶቼን ሁሉ እሰጥሃለሁ፤ እኔ በምሰጣቸው ምድር እነዚህን ሕግጋቴን፥ ትእዛዞች ሥርዓቶቼን በመጠበቅ እንዲኖሩ ለሕዝቡ አስተምራቸው።’
32“ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ ያዘዛችሁን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ሁኑ፤ ከሕግጋቱም አንዱን እንኳ አትጣሱ፤ 33ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ እንዲከናወንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ለረጅም ዘመናት እንድትኖሩ፥ እግዚአብሔር ያዘዛችሁን ሁሉ ፈጽሙ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 5: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: