ወደ ገላትያ ሰዎች 4
4
የእግዚአብሔር ልጆች ስለ መሆናችን
1አሁንም የምለው ይህን ነው፤ ወራሹ ሕፃን ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ ምንም እንኳ የንብረቱ ሁሉ ጌታ ቢሆን ከባሪያ በምንም አይለይም። 2ነገር ግን አባቱ የወሰነለት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በሞግዚቶችና በመጋቢዎች ሥር ነው። 3እንዲሁም እኛ በመንፈሳዊ ነገር እንደ ሕፃናት በነበርንበት ጊዜ ለዚህ ዓለም ሥርዓት ተገዢዎች ሆነን ባሪያዎች ነበርን። 4ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከልን፤ እርሱ ከሴት ተወለደ፤ ለሕግም ታዛዥ ሆነ። 5ይህንንም ያደረገው ከሕግ ሥር ያሉትን ለመዋጀትና እኛም የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆን ለማድረግ ነው። #ሮም 8፥15-17።
6የእግዚአብሔር ልጆች በመሆናችንም እግዚአብሔርን “አባባ” እያለ የሚጠራውን የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ። 7ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅ ከሆንክም የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።
ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች የነበረው ጭንቀት
8ከዚህ በፊት እግዚአብሔርን ባለማወቃችሁ ምክንያት በባሕርያቸው አማልክት ላልሆኑት ባሪያዎች ሆናችሁ ትገዙ ነበር። 9አሁን ግን እግዚአብሔርን ዐውቃችኋል፤ ይልቁንም እግዚአብሔር እናንተን ዐውቋችኋል፤ ታዲያ፥ ወደ እነዚያ ወደ ደካሞችና ወደማይረቡት የዓለም ሥርዓቶች እንዴት ተመለሳችሁ? እንዴትስ እንደገና የእነርሱ ባሪያዎች ለመሆን ትፈልጋላችሁ? 10ለተለዩ ቀኖችና ወሮች ለተወሰኑ የዓመት ክፍሎችና ዓመቶች ጥንቃቄ በማድረግ ልዩ ክብር ትሰጣላችሁ። 11በእናንተ መካከል በሥራ የደከምኩበት ድካም ሁሉ ከንቱ ሆኖ ይቀራል ብዬ እፈራለሁ።
12ወንድሞች ሆይ! እኔ እንደ እናንተ ስለ ሆንኩ እናንተም እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ፤ እናንተ ምንም አልበደላችሁኝም። 13በመጀመሪያ ጊዜ የምሥራቹን ቃል ለእናንተ ለመስበክ ዕድል ያገኘሁት በሕመም ላይ በነበርኩበት ጊዜ መሆኑን ታውቃላችሁ። 14ምንም እንኳ ሕመሜ ፈተና ቢሆንባችሁ አልናቃችሁኝም ወይም አልተጸየፋችሁኝም፤ እንዲያውም የእግዚአብሔርን መልአክ እንደምትቀበሉ አድርጋችሁ ተቀበላችሁኝ፤ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትቀበሉ አድርጋችሁ ተቀበላችሁኝ። 15ከዚህ በፊት የነበራችሁ ደስታ ሁሉ የት ሄደ? ቢቻልስ ዐይኖቻችሁን እንኳ አውጥታችሁ ትሰጡኝ እንደ ነበረ እኔ ራሴ እመሰክርላችኋለሁ። 16ታዲያ፥ አሁን እውነትን ስለ ነገርኳችሁ ጠላታችሁ ሆኜ ተገኘሁን?
17ሌሎች ሰዎች ስለ እናንተ በመጨነቅ ያስባሉ፤ ይሁን እንጂ ይህን የሚያደርጉት ለመልካም አይደለም፤ የእነርሱ ፍላጎት እናንተ ከእኛ እንድትለዩና ለእነርሱ በትጋት እንድታስቡ ነው። 18ዓላማው ጥሩ ከሆነ መትጋት ምንጊዜም መልካም ነው፤ ነገር ግን ይህ መትጋታችሁ እኔ ከእናንተ ጋር በምኖርበት ጊዜ ብቻ አይሁን። 19ልጆቼ ሆይ! ክርስቶስ በእናንተ ላይ ተቀርጾ እስኪታይ ድረስ እንደገና ስለ እናንተ በምጥ ጭንቅ ላይ እገኛለሁ። 20ከበፊቱ የተለየ ሁኔታ እንዳሳያችሁ አሁን ከእናንተ ጋር መሆን በፈለግሁ ነበር፤ ነገር ግን ምን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ባለማወቄ ግራ ገብቶኝ ተጨንቄአለሁ።
የአጋርና የሣራ ምሳሌነት
21እናንተ ለሕግ ተገዢዎች ሆናችሁ መኖር የምትፈልጉ እስቲ ንገሩኝ፤ ሕግ የሚለውን አትሰሙምን? 22በቅዱሳት መጻሕፍት “አብርሃም ሁለት ልጆች ነበሩት፤ አንደኛው የተወለደው ከአገልጋይቱ ሴት ሲሆን ሌላው የተወለደው ከነጻይቱ ሴት ነበር” ተብሎ ተጽፎአል። 23የአገልጋይቱ ልጅ የተወለደው በሥጋዊ ልማድ ሲሆን የነፃይቱ ልጅ የተወለደው ግን በተሰጠው ተስፋው ቃል መሠረት ነበር። 24ይህም ምሳሌ ነበር፤ እነዚህ ሁለት ሴቶች የሁለት ኪዳኖች ምሳሌ ነበሩ፤ ከሲና ተራራ የሆነችው የአንደኛዋ ምሳሌ አጋር ናት፤ እርስዋ ልጆችን የምትወልደው ለባርነት ነበር። #ዘፍ. 16፥15፤ 21፥2። 25አጋር በዐረብ አገር ለሚገኘው ለሲና ተራራ ምሳሌ ነበረች፤ ስለዚህ ከአሁኒቱ ኢየሩሳሌም ጋር ትመሳሰላለች፤ እርስዋ ከነልጆችዋ በባርነት የምትገኝ ናት። 26ከላይ ከሰማይ የሆነችው ኢየሩሳሌም ግን ነጻ ናት፤ እርስዋ የሁላችን እናት ናት።
27“አንቺ ልጆች የማትወልጂ መኻን ደስ ይበልሽ!
አንቺ ለመውለድ አምጠሽ የማታውቂ ‘እልል!’ በዪ፤
ባል ካላት ሴት ይልቅ
ባል የሌላት ሴት ብዙ ልጆች አሉአት” ተብሎ ተጽፎአል። #ኢሳ. 54፥1።
28ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተም እንደ ይስሐቅ የተስፋው ቃል ልጆች ናችሁ። 29ነገር ግን በዚያን ጊዜ በሥጋ የተወለደው በመንፈስ የተወለደውን እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው። #ዘፍ. 21፥9። 30ነገር ግን ቅዱስ መጽሐፍ የሚለው ምንድን ነው? ቅዱስ መጽሐፍ “አገልጋይቱ ሴት የወለደችው ልጅ ነጻይቱ ሴት ከወለደችው ልጅ ጋር አብሮ ስለማይወርስ አገልጋይቱን ከነልጅዋ ወዲያ አስወጣት” ይላል። #ዘፍ. 21፥10። 31ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ፥ እኛ የነፃይቱ ልጆች ነን እንጂ የአገልጋይቱ ልጆች አይደለንም።
Currently Selected:
ወደ ገላትያ ሰዎች 4: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: