ወደ ገላትያ ሰዎች መግቢያ
መግቢያ
ስለ ኢየሱስ አዳኝነት የሚናገረው የወንጌል ቃል በየቦታው እየተሰበከ አይሁድ ያልሆኑ ሰዎች እየተቀበሉት በሄዱ መጠን “ክርስቲያን ለመሆን የኦሪትን ሕግ መፈጸም ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም?” የሚለውም ጥያቄ አብሮ ተነሣ፤ በታናሽቱ እስያ የሮም ግዛት በሆነችው በገላትያ ባሉ አብያተ ክርስቲያን መካከል “ሰው በእግዚአብሔር ፊት እንዲጸድቅ በኢየሱስ ማመን ብቻ ሳይሆን በሙሴም አማካይነት የተሰጠውን ሕግ መፈጸም አለበት” በማለት ጳውሎስን የሚቃወሙ ሰዎች ነበሩ።
ጳውሎስ ይህን የገላትያን መልእክት የጻፈው በዚህ ትምህርት ግራ የተጋቡትን ሰዎች ወደ ትክክለኛው እምነትና የክርስትና ሕይወት ለመምራት ነው፤ ጳውሎስ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ መሆኑን በማረጋገጥ ይጀምራል፤ ለሐዋርያነት የጠራው እግዚአብሔር እንጂ ሰው እንዳልሆነና የእርሱም ተልእኮ አይሁድ ወዳልሆኑ ሰዎች እንደ ሆነ በመዘርዘር ያስረዳል፤ በመጨረሻዎቹ ምዕራፎች ውስጥ ክርስቲያናዊ ሕይወት በኢየሱስ ከማመን ከሚገኘው ፍቅር የሚመነጭ መሆኑን ያስረዳል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1-10
የጳውሎስ ሐዋርያዊ ሥልጣን 1፥11—2፥21
የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌል 3፥1—4፥31
ክርስቲያናዊ ነጻነትና እምነት 5፥1—6፥10
መደምደሚያ 6፥11-18
Currently Selected:
ወደ ገላትያ ሰዎች መግቢያ: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: