YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘፍጥረት 10

10
የኖኅ ልጆች ትውልድ
(1ዜ.መ. 1፥5-23)
1የኖኅ ልጆች የሴም፥ የካምና የያፌት ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፤ እነዚህ ሦስቱ ከጥፋት ውሃ በኋላ ልጆችን ወለዱ፤
የያፌት ዘሮች
2የያፌት ልጆች፦ ጎሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ያዋን፥ ቱባል፥ ሜሼክና፥ ቲራስ ናቸው። 3የጎሜር ልጆች፦ አሽከናዝ፥ ሪፋትና ቶጋርማ ናቸው። 4የያዋን ልጆች፦ የኤሊሻ፥ የተርሴስ፥ የኪቲምና የሮዳኒም ሰዎች ናቸው። #10፥4 ተርሴስ፦ ዛሬ “እስፔን” የምትባለው አገር ነች። #10፥4 ኪቲም፦ ዛሬ “ቆጵሮስ” የምትባለው ደሴት ነች። #10፥4 ሮዳኒም፦ ዛሬ “ሮድ” የምትባለው ደሴት ነች።
5እነዚህ ሁሉ በባሕር ዳርቻና በደሴቶች ላይ ለሚኖሩ የያፌት ዘሮች ቅድመ አያቶች ናቸው፤ በየአገራቸውና በየጐሣቸውም ተከፋፍለው የሚኖሩ ሕዝቦች ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገርበት የራሱ ቋንቋ ነበረው።
የካም ዘሮች
6የካም ልጆች፦ ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥና ከነዓን ናቸው። 7የኩሽ ልጆች፦ ሳባ፥ ሐዊላ፥ ሳብታ፥ ራዕማና ሳብተካ ናቸው። የራማ ልጆች፥ ሳባና ደዳን ናቸው። #10፥7 ምጽራይም፦ ዛሬ “ግብጽ” የምትባለው አገር ነች። #10፥7 ፉጥ፦ ዛሬ “ሊብያ” የምትባለው አገር ነች።
8ኩሽ በዓለም ላይ የመጀመሪያው ታላቅ ጦረኛ የነበረውን ናምሩድን ወለደ። 9ናምሩድ በእግዚአብሔር ድጋፍ ታላቅ አዳኝ ነበረ፤ ሰዎች “እንደ ናምሩድ ታላቅ አዳኝ ያድርግህ!” እያሉ የሚመርቁት ስለዚህ ነው። 10በመጀመሪያ የናምሩድ መንግሥት በሰናዖር የነበሩትን የሦስት ከተሞች ግዛት ማለትም ባቢሎን፥ ኤሬክንና አካድን ያጠቃልል ነበር። 11ከዚያም ወደ አሦር ሄደና ነነዌን፥ ረሖቦትን፥ ካላሕን መሠረተ፤ 12እንዲሁም በነነዌና በካላሕ መካከል ያለውን ታላቅ ከተማ ሬሴን የተባሉትን ከተሞች መሠረተ።
13የምጽራይም ዘሮች ሉድ፥ ዐናማውያን፥ ለሃባውያን፥ ናፍሐውያን፥ 14ፈትሮሳውያን፥ ከስሉሃውያን ሲሆኑ ከእነርሱም ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው የካፍቶር ሕዝቦች ናቸው።
15የከነዓን ልጆች በኲሩ ጺዶን፥ ተከታዩ ሔት ይባሉ ነበር፤ 16ሌሎቹም የከነዓን ዘሮች ኢያቡሳውያን፥ አሞራውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ 17ሒዋውያን፥ ዓርቃውያን፥ ሲናውያን፥ 18አርዋዳውያን፥ ጸማራውያን፥ ሐማታውያን ነበሩ፤ ዘግይቶም የተለያዩት የከነዓን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤ 19በዚህ ዐይነት የከነዓናውያን ድንበር ከሲዶና አንሥቶ በስተደቡብ በገራር አጠገብ እስካለው እስከ ጋዛ ድረስ፥ በስተ ምሥራቅ እስከ ሰዶም፥ ገሞራ፥ አዳማና በላሻዕ አጠገብ እስካለው እስከ ጸቦይም ድረስ ሆነ። 20እነዚህ ሁሉ የካም ዘሮች ናቸው፤ እነርሱ በተለያዩ ጐሣዎችና አገሮች ተከፍለው ይኖሩ ነበር፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገረው በራሱ ቋንቋ ነበር።
የሴም ዘሮች
21የያፌት ታላቅ ወንድም ሴም የዔቦር ዘሮች ቅድመ አያት ነው።
22የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድና አራም ናቸው። 23የአራም ልጆች፦ ዑፅ፥ ሑል፥ ጌተርና ሜሼክ ናቸው፤ 24አርፋክስድ ሼላሕን ወለደ፤ ሼላሕም ዔቦርን ወለደ። 25ዔቦር ሁለት ልጆች ወለደ፤ አንደኛው እርሱ በተወለደበት ዘመን ሕዝቦች ስለ ተከፋፈሉ ፋሌቅ ተባለ፤ ሌላው ዮቅጣን ይባል ነበር። #10፥25 ፋሌቅ፦ በዕብራይስጥ “መከፋፈል” ማለት ነው። 26የዮቅጣን ልጆች፦ አልሞዳድ፥ ሼሌፍ ሐጻርማዌት፥ ዬራሕ፥ 27ሀዶራም፥ ኡዛል፥ ዲቅላ፥ 28ዖባል፥ አቢማኤል፥ ሳባ፥ 29ኦፊር፥ ሐዊላና ዮባብ ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ዘሮች ናቸው።
30እነርሱ የኖሩበት ምድር በስተምሥራቅ ባለው በተራራማው አገር ከሜሻ እስከ ሰፋር ይደርስ ነበር። 31እነዚህ ሁሉ የሴም ዘሮች ናቸው፤ እነርሱ በተለያዩ ጐሣዎችና አገሮች ተከፍለው ይኖሩ ነበር፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገረው በራሱ ቋንቋ ነበር።
32እነዚህ በየነገዳቸው የተከፋፈሉ ሕዝቦች የኖኅ ዘሮች ነበሩ፤ ከጥፋት ውሃ በኋላ የምድር ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከእነዚህ ከኖኅ ልጆች ነበር።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for ኦሪት ዘፍጥረት 10