ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 11:24-27
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 11:24-27 አማ05
ሙሴም ካደገ በኋላ “የፈርዖን የልጅ ልጅ” ተብሎ መጠራትን ያልፈቀደው በእምነት ነው፤ ስለዚህም እርሱ በኃጢአት ከሚገኘው ጊዜያዊ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ። ወደፊትም የሚቀበለውን ዋጋ ስለ ተመለከተ ከግብጽ ሀብት ይልቅ ስለ መሲሑ መዋረድ የበለጠ መሆኑን አሰበ። የንጉሡንም ቊጣ ሳይፈራ ከግብጽ የወጣው በእምነት ነው፤ በዐይን የማይታየውንም አምላክ እንዳየው ያኽል ሆኖ በዓላማው ጸና።