ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 8
8
የኢየሱስ የአዲስ ኪዳን የካህናት አለቃ መሆን
1እንግዲህ ከምንነጋገርባቸው ነገሮች ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማይ በልዑል እግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ የካህናት አለቃ አለን፤ #መዝ. 110፥1። 2እርሱ የሚያገለግለው እውነተኛ ድንኳን በሆነችው መቅደስ ነው፤ ይህች ድንኳን የተተከለችው በሰው እጅ ሳይሆን በጌታ ነው። 3እያንዳንዱ የካህናት አለቃ የሚሾመው መባንና መሥዋዕትን ለማቅረብ ነው፤ ስለዚህ ይህም ካህን የሚያቀርበው አንድ ነገር ሊኖረው ያስፈልጋል። 4በሕግ መሠረት መባን የሚያቀርቡ ካህናት ስላሉ እርሱ በምድር ቢሆን ኖሮ ካህን ባልሆነም ነበር፤ 5እነዚህ ካህናት የሚያገለግሉበት ድንኳን በሰማይ ለሚገኘው ምሳሌና ጥላ ብቻ ነው፤ ይህም የሆነው ሙሴ ድንኳኒቱን በሚሠራበት ጊዜ፤ እግዚአብሔር “በተራራው ላይ እንደ ተገለጠልህ ዐይነት ሁሉን ነገር በጥንቃቄ አድርግ” ብሎ ባዘዘው መሠረት ነው። 6አሁን ግን ኢየሱስ አማካይ አስማሚ የሆነበት ቃል ኪዳን ከአሮጌው ቃል ኪዳን የበለጠና በተሻለ ተስፋ ላይ የተመሠረተ እንደ መሆኑ ለእርሱ የተሰጠው አገልግሎት የበለጠ ነው።
7የመጀመሪያው ቃል ኪዳን ነቀፋ የሌለው ሆኖ ቢገኝ ኖሮ ሁለተኛው ቃል ኪዳን ባላስፈለገ ነበር። 8እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ነቀፋ መኖሩን በማመልከት እንዲህ ይላል፦
“እነሆ፥ ከእስራኤል ሕዝብና ከይሁዳ ሕዝብ ጋር
አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ጌታ። #ኤር. 31፥31-34።
9ይህም ቃል ኪዳን እጃቸውን ይዤ ከግብጽ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ቃል ኪዳን ያለ አይደለም፤ እነርሱ በቃል ኪዳኔ ስላልጸኑ እኔም ችላ አልኳቸው ይላል ጌታ።
10“እነሆ፥ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር
የምገባው ቃል ኪዳን የሚከተለው ነው ይላል ጌታ፤
እኔ ሕጌን በአእምሮአቸው አኖራለሁ፤
በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤
አምላካቸውም እሆናለሁ፤
እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
11‘ጌታን ዕወቅ’ ብሎ ጎረቤቱን ሆነ
ወንድሙን የሚያስተምር ማንም አይኖርም፤
ከትንሹ ጀምሮ እስከ ትልቁ ሁሉም
ያውቀኛል፤
12በደላቸውን ይቅር እልላቸዋለሁ፤
ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስባቸውም።”
13እንግዲህ “አዲስ ቃል ኪዳን” ሲል የፊተኛውን ቃል ኪዳን አሮጌ አድርጎታል ማለት ነው፤ ስለዚህ የተሠራበትና አሮጌው ነገር ሁሉ የሚጠፋበት ጊዜ ተቃርቧል።
Currently Selected:
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 8: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: