ትንቢተ ኢሳይያስ 40
40
ተስፋ የተሞላበት ቃል
1እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲህ ይላል፦
“ሕዝቤን አጽናኑ! ሕዝቤን አጽናኑ!
2የባርነት ጊዜዋ እንዳለቀ፥ ለፈጸመችው ኃጢአት ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ እጥፍ ቅጣት እንደ ተቀበለችና ኃጢአትዋም ይቅር እንደ ተባለላት ለኢየሩሳሌም በለሰለሰ አነጋገር ንገሯት።”
3እንዲህ የሚል ድምፅ ይሰማል፦
“በምድረ በዳ የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ!
በበረሓም ለአምላካችን ጥርጊያ ጐዳና አብጁ! #ማቴ. 3፥3፤ ማር. 1፥3፤ ዮሐ. 1፥23።
4ጐድጓዳውና ሸለቆው ይሙላ፤
ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ብሎ ይደልደል፤
ኮረብታውና ወጣ ገባ የሆነው ምድር ሁሉ ይስተካከል።
5በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ክብር ይገለጣል፤
እግዚአብሔር ይህን የተናገረ ስለ ሆነ
ሰዎች ሁሉ ይህን በአንድነት ሆነው ያዩታል።” #ሉቃ. 3፥4-6።
6አንድ ድምፅ “የዐዋጅ ቃል ተናገር!” እያለ ይጮኻል።
እኔም “ምን ብዬ ላውጅ!” ስል ጠየቅሁ።
ያም ድምፅ “እንዲህ ብለህ ዐውጅ” አለኝ፦
“ሰው ሁሉ እንደ ሣር ነው፤
ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው፤
7የእግዚአብሔር ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ፥
ሣሩ እንደሚደርቅና አበባውም እንደሚረግፍ
ሰውም እንዲሁ ረጋፊ ነው።
8በእርግጥ ሣር ይደርቃል፤ አበባም ይረግፋል፤
የአምላካችን ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።” #ያዕ. 1፥10-11፤ 1ጴጥ. 1፥24-25።
9ለጽዮን መልካም ነገርን የምታበሥሩ ሆይ!
ወደ ከፍተኛ ተራራ ውጡ!
እናንተ ለኢየሩሳሌም መልካም ዜናን የምታበሥሩ ሆይ!
ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ!
ጮክ በሉ አትፍሩ!
ለይሁዳ ከተሞች፥ “እነሆ፥ አምላካችሁ” በሉ።
10እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ለመግዛት ይመጣል፤
የሚመጣውም የሚሰጠውን ሽልማትና የሚከፍለውን የሥራ ዋጋ ይዞ ነው።
#
ኢሳ. 62፥11፤ ራዕ. 22፥12። 11እንደ እረኛ ለመንጋው እንክብካቤ ያደርጋል፤
ግልገሎቹን በአንድነት ይሰበስባል፤
በእጆቹም ዐቅፎ ይወስዳቸዋል፤
እናቶቻቸውንም በርኅራኄ ይመራቸዋል። #ሕዝ. 34፥15፤ ዮሐ. 10፥11።
እግዚአብሔርን ማን ይወዳደራል?
12ውቅያኖስን በእፍኙ፥ ሰማይንም በስንዝሩ፥
የምድርን ዐፈር በቊና መለካት የሚችል ማን ነው?
ተራራዎችንና ኰረብቶችንስ
በሚዛን የሚመዝን ማን ነው?
13እግዚአብሔርን “እንዲህ አድርግ” ብሎ የሚያዘው ማን ነው?
እርሱን ማስተማርና መምከር የሚችልስ ማን ነው? #ሮም 11፥34፤ 1ቆሮ. 2፥16።
14ያብራራለት ዘንድ እግዚአብሔር ማንን አማከረ?
ትክክለኛውን ፍርድ ያስተማረው ማነው?
ዕውቀትን ያስተማረው፥ ወይም ትክክለኛውን መንገድ እንዲያስተውል ያደረገው ማነው?
15በእግዚአብሔር ፊት ሕዝቦች እንደ አንድ የውሃ ጠብታ ናቸው፤
በሚዛንም ላይ እንዳለ ዐቧራ ናቸው፤
ደሴቶችም በእርሱ ዘንድ እንደ ትቢያ የቀለሉ ናቸው።
16በሊባኖስ የሚገኙ እንስሳት ሁሉ ለአምላካችን
የሚቃጠል መሥዋዕት ለመሆን፥
ከሚፈለገው ቊጥር ያነሱ ናቸው።
ዛፎቹም ሁሉ የመሥዋዕቱን እሳት ለማቀጣጠል አይበቁም።
17በእግዚአብሔር ዘንድ ሕዝቦች ሁሉ
እንዳሉ የሚቈጠሩ አይደሉም።
እነርሱ በእርሱ ዘንድ እንደ ኢምንት የሚቈጠሩና
ዋጋ የሌላቸው ናቸው።
18እግዚአብሔርን ከማን ጋር ታነጻጽሩታላችሁ?
ከማንስ ጋር ታመሳስሉታላችሁ?
19እርሱ እኮ እንጨት ጠራቢ እንደሚቀርጸው፥
አንጥረኛም በወርቅ እንደሚለብጠው
በብር ሠርቶ እንደሚያቆመው ጣዖት ዐይነት አይደለም። #ሐ.ሥ. 17፥29።
20ሀብት የሌለው ድኻ ለመባው በማይነቅዝ ልዩ እንጨት
ይመርጥና በግንባሩ እንዳይደፋ
ብልኀተኛ አስተካክሎ
እንዲሠራው ያደርጋል።
21ከቶ ይህን አታውቁምን? አልሰማችሁምን?
ከመጀመሪያው ጀምሮ አልተነገራችሁምን?
ምድር ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ አላስተዋላችሁምን?
22እግዚአብሔር ከምድር ክበብ በላይ ዙፋኑን ዘርግቶ መቀመጡን
ሰማይን እንደ መጋረጃ መወጠሩንና፥ እንደ መኖሪያ ድንኳን መዘርጋቱን
የምድርም ሕዝቦች እንደ ፌንጣ አነስተኞች መሆናቸውን።
23እርሱ ልዑላንን ያዋርዳል፤
የዚህ ዓለም ገዢዎችንም እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል።
24እነርሱ ገና እንደ በቀለና ሥር እንዳልሰደደ አዲስ ተክል ናቸው፤
እግዚአብሔር ነፋሱን ሲልክ ወዲያውኑ ይደርቃሉ፤
እንደ ገለባም በነው ይጠፋሉ።
25“ታዲያ፥ እኔን ከማን ጋር ታነጻጽሩኛላችሁ?
ከማንስ ጋር ታመሳስሉኛላችሁ?” ይላል ቅዱስ እግዚአብሔር።
26ቀና ብላችሁ ወደ ሰማይ ተመልከቱ፤
የምታዩአቸውን ከዋክብት የፈጠረ ማን ነው?
እርሱ እንደ ጦር ሠራዊት ይመራቸዋል፤
ምን ያኽል እንደ ሆኑም ቊጥራቸውን ያውቃል፤
እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል፤
የእርሱ ሥልጣንና ኀይል እጅግ ታላቅ ነው፤
ስለዚህ ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይጠፋም።
27የያዕቆብ ዘር የእስራኤል ሕዝብ ሆይ!
“አካሄዴ ከእግዚአብሔር የተሰወረ ነው፤
መብቴም በእርሱ ዘንድ ችላ ተብሎብኛል፤”
ብለህ ለምን ታማርራለህ?
28ከቶ አታውቅምን? ከቶስ አልሰማህምን?
እግዚአብሔር የዘለዓለም አምላክ ነው፤
ዓለምን ሁሉ የፈጠረ እርሱ ነው፤
እርሱ ከቶ አይደክምም ወይም አይታክትም፤
ሐሳቡን መርምሮ ሊደርስበት የሚቻለው የለም።
29እርሱ ለደከሙት ብርታትን ይሰጣል፤
ለዛሉትም ኀይልን ይጨምራል።
30ወጣቶች እንኳ ይደክማሉ፥ ይታክታሉም፤
ጐልማሶችም ዝለው ይወድቃሉ፤
31በእግዚአብሔር ተማምነው የሚኖሩ ግን
ኀይላቸው ይታደስላቸዋል።
እንደ ንሥር በክንፍ ይበራሉ፤
ይሮጣሉ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ አይደክሙም።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 40: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
ትንቢተ ኢሳይያስ 40
40
ተስፋ የተሞላበት ቃል
1እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲህ ይላል፦
“ሕዝቤን አጽናኑ! ሕዝቤን አጽናኑ!
2የባርነት ጊዜዋ እንዳለቀ፥ ለፈጸመችው ኃጢአት ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ እጥፍ ቅጣት እንደ ተቀበለችና ኃጢአትዋም ይቅር እንደ ተባለላት ለኢየሩሳሌም በለሰለሰ አነጋገር ንገሯት።”
3እንዲህ የሚል ድምፅ ይሰማል፦
“በምድረ በዳ የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ!
በበረሓም ለአምላካችን ጥርጊያ ጐዳና አብጁ! #ማቴ. 3፥3፤ ማር. 1፥3፤ ዮሐ. 1፥23።
4ጐድጓዳውና ሸለቆው ይሙላ፤
ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ብሎ ይደልደል፤
ኮረብታውና ወጣ ገባ የሆነው ምድር ሁሉ ይስተካከል።
5በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ክብር ይገለጣል፤
እግዚአብሔር ይህን የተናገረ ስለ ሆነ
ሰዎች ሁሉ ይህን በአንድነት ሆነው ያዩታል።” #ሉቃ. 3፥4-6።
6አንድ ድምፅ “የዐዋጅ ቃል ተናገር!” እያለ ይጮኻል።
እኔም “ምን ብዬ ላውጅ!” ስል ጠየቅሁ።
ያም ድምፅ “እንዲህ ብለህ ዐውጅ” አለኝ፦
“ሰው ሁሉ እንደ ሣር ነው፤
ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው፤
7የእግዚአብሔር ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ፥
ሣሩ እንደሚደርቅና አበባውም እንደሚረግፍ
ሰውም እንዲሁ ረጋፊ ነው።
8በእርግጥ ሣር ይደርቃል፤ አበባም ይረግፋል፤
የአምላካችን ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።” #ያዕ. 1፥10-11፤ 1ጴጥ. 1፥24-25።
9ለጽዮን መልካም ነገርን የምታበሥሩ ሆይ!
ወደ ከፍተኛ ተራራ ውጡ!
እናንተ ለኢየሩሳሌም መልካም ዜናን የምታበሥሩ ሆይ!
ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ!
ጮክ በሉ አትፍሩ!
ለይሁዳ ከተሞች፥ “እነሆ፥ አምላካችሁ” በሉ።
10እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ለመግዛት ይመጣል፤
የሚመጣውም የሚሰጠውን ሽልማትና የሚከፍለውን የሥራ ዋጋ ይዞ ነው።
#
ኢሳ. 62፥11፤ ራዕ. 22፥12። 11እንደ እረኛ ለመንጋው እንክብካቤ ያደርጋል፤
ግልገሎቹን በአንድነት ይሰበስባል፤
በእጆቹም ዐቅፎ ይወስዳቸዋል፤
እናቶቻቸውንም በርኅራኄ ይመራቸዋል። #ሕዝ. 34፥15፤ ዮሐ. 10፥11።
እግዚአብሔርን ማን ይወዳደራል?
12ውቅያኖስን በእፍኙ፥ ሰማይንም በስንዝሩ፥
የምድርን ዐፈር በቊና መለካት የሚችል ማን ነው?
ተራራዎችንና ኰረብቶችንስ
በሚዛን የሚመዝን ማን ነው?
13እግዚአብሔርን “እንዲህ አድርግ” ብሎ የሚያዘው ማን ነው?
እርሱን ማስተማርና መምከር የሚችልስ ማን ነው? #ሮም 11፥34፤ 1ቆሮ. 2፥16።
14ያብራራለት ዘንድ እግዚአብሔር ማንን አማከረ?
ትክክለኛውን ፍርድ ያስተማረው ማነው?
ዕውቀትን ያስተማረው፥ ወይም ትክክለኛውን መንገድ እንዲያስተውል ያደረገው ማነው?
15በእግዚአብሔር ፊት ሕዝቦች እንደ አንድ የውሃ ጠብታ ናቸው፤
በሚዛንም ላይ እንዳለ ዐቧራ ናቸው፤
ደሴቶችም በእርሱ ዘንድ እንደ ትቢያ የቀለሉ ናቸው።
16በሊባኖስ የሚገኙ እንስሳት ሁሉ ለአምላካችን
የሚቃጠል መሥዋዕት ለመሆን፥
ከሚፈለገው ቊጥር ያነሱ ናቸው።
ዛፎቹም ሁሉ የመሥዋዕቱን እሳት ለማቀጣጠል አይበቁም።
17በእግዚአብሔር ዘንድ ሕዝቦች ሁሉ
እንዳሉ የሚቈጠሩ አይደሉም።
እነርሱ በእርሱ ዘንድ እንደ ኢምንት የሚቈጠሩና
ዋጋ የሌላቸው ናቸው።
18እግዚአብሔርን ከማን ጋር ታነጻጽሩታላችሁ?
ከማንስ ጋር ታመሳስሉታላችሁ?
19እርሱ እኮ እንጨት ጠራቢ እንደሚቀርጸው፥
አንጥረኛም በወርቅ እንደሚለብጠው
በብር ሠርቶ እንደሚያቆመው ጣዖት ዐይነት አይደለም። #ሐ.ሥ. 17፥29።
20ሀብት የሌለው ድኻ ለመባው በማይነቅዝ ልዩ እንጨት
ይመርጥና በግንባሩ እንዳይደፋ
ብልኀተኛ አስተካክሎ
እንዲሠራው ያደርጋል።
21ከቶ ይህን አታውቁምን? አልሰማችሁምን?
ከመጀመሪያው ጀምሮ አልተነገራችሁምን?
ምድር ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ አላስተዋላችሁምን?
22እግዚአብሔር ከምድር ክበብ በላይ ዙፋኑን ዘርግቶ መቀመጡን
ሰማይን እንደ መጋረጃ መወጠሩንና፥ እንደ መኖሪያ ድንኳን መዘርጋቱን
የምድርም ሕዝቦች እንደ ፌንጣ አነስተኞች መሆናቸውን።
23እርሱ ልዑላንን ያዋርዳል፤
የዚህ ዓለም ገዢዎችንም እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል።
24እነርሱ ገና እንደ በቀለና ሥር እንዳልሰደደ አዲስ ተክል ናቸው፤
እግዚአብሔር ነፋሱን ሲልክ ወዲያውኑ ይደርቃሉ፤
እንደ ገለባም በነው ይጠፋሉ።
25“ታዲያ፥ እኔን ከማን ጋር ታነጻጽሩኛላችሁ?
ከማንስ ጋር ታመሳስሉኛላችሁ?” ይላል ቅዱስ እግዚአብሔር።
26ቀና ብላችሁ ወደ ሰማይ ተመልከቱ፤
የምታዩአቸውን ከዋክብት የፈጠረ ማን ነው?
እርሱ እንደ ጦር ሠራዊት ይመራቸዋል፤
ምን ያኽል እንደ ሆኑም ቊጥራቸውን ያውቃል፤
እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል፤
የእርሱ ሥልጣንና ኀይል እጅግ ታላቅ ነው፤
ስለዚህ ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይጠፋም።
27የያዕቆብ ዘር የእስራኤል ሕዝብ ሆይ!
“አካሄዴ ከእግዚአብሔር የተሰወረ ነው፤
መብቴም በእርሱ ዘንድ ችላ ተብሎብኛል፤”
ብለህ ለምን ታማርራለህ?
28ከቶ አታውቅምን? ከቶስ አልሰማህምን?
እግዚአብሔር የዘለዓለም አምላክ ነው፤
ዓለምን ሁሉ የፈጠረ እርሱ ነው፤
እርሱ ከቶ አይደክምም ወይም አይታክትም፤
ሐሳቡን መርምሮ ሊደርስበት የሚቻለው የለም።
29እርሱ ለደከሙት ብርታትን ይሰጣል፤
ለዛሉትም ኀይልን ይጨምራል።
30ወጣቶች እንኳ ይደክማሉ፥ ይታክታሉም፤
ጐልማሶችም ዝለው ይወድቃሉ፤
31በእግዚአብሔር ተማምነው የሚኖሩ ግን
ኀይላቸው ይታደስላቸዋል።
እንደ ንሥር በክንፍ ይበራሉ፤
ይሮጣሉ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ አይደክሙም።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997