የዮሐንስ ወንጌል 12
12
ኢየሱስን ሽቶ የቀባች ሴት
(ማቴ. 26፥6-13፤ ማር. 14፥3-9)
1የአይሁድ የፋሲካ በዓል ሊከበር ስድስት ቀን ሲቀረው፥ ኢየሱስ ወደ ቢታንያ ሄደ፤ ቢታንያ ኢየሱስ ከሞት ያስነሣው አልዓዛር የሚኖርባት መንደር ነች። 2በዚያ ራት አዘጋጁለት፤ ማርታ ታገለግል ነበር፤ አልዓዛርም ከኢየሱስ ጋር በማእድ ቀርበው ከነበሩት አንዱ ነበር። 3በዚያን ጊዜ ማርያም ዋጋው እጅግ የከበረ ከንጹሕ ናርዶስ የተሠራ፥ ግማሽ ሊትር የሚሆን አንድ ብልቃጥ ሽቶ ወስዳ፥ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ በጠጒርዋም አበሰቻቸው፤ ቤቱም በሽቶው መዓዛ ተሞላ። #ሉቃ. 7፥37-38። 4ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ ኢየሱስን አሳልፎ የሚሰጠው አስቆሮታዊው ይሁዳ፥ 5“ይህ ሽቶ በሦስት መቶ ዲናር ተሸጦ ገንዘቡ ለድኾች ለምን አልተሰጠም?” አለ። #12፥5 ዲናር፦ የቀን ሠራተኛ የአንድ ቀን ደመወዝ ነው። 6እርሱ ይህን የተናገረው፥ ለድኾች አዝኖ ሳይሆን፥ ሌባ ስለ ነበረ ነው፤ የገንዘብ ከረጢት የሚይዝ እርሱ በመሆኑ በከረጢቱ የሚከተተውን ገንዘብ መውሰድ ለምዶ ነበር።
7ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “ለምቀበርበት ቀን ያደረገችው ዝግጅት ስለ ሆነ ተዉአት። 8ድኾች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልሆንም።” #ዘዳ. 15፥11።
9በዚያን ጊዜ ከአይሁድ ብዙዎች ኢየሱስ በቢታንያ መሆኑን ዐውቀው መጡ፤ የመጡትም ስለ ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ከሞት ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር። 10የካህናት አለቆች ግን አልዓዛርንም ለመግደል ተማከሩ። 11በእርሱ የተነሣ ከአይሁድ ብዙዎቹ እምነታቸውን እየተዉ በኢየሱስ ያምኑ ስለ ነበረ ነው።
የኢየሱስ በታላቅ ክብር ወደ ኢየሩሳሌም መግባት
(ማቴ. 21፥1-11፤ ማር. 11፥1-11፤ ሉቃ. 19፥28-40)
12በማግስቱ ለፋሲካ በዓል የመጡ ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም የሚመጣ መሆኑን ሰሙ። 13ስለዚህ የዘንባባ ቅርንጫፍ ይዘው ሊቀበሉት ወጡ፤ “ሆሳዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው!” እያሉ ይጮኹ ነበር። #መዝ. 118፥25-26።
14ኢየሱስ የአህያ ውርንጭላ አገኘና በእርሱ ላይ ተቀመጠ፤ ይህም የሆነው፥
15“አንቺ የጽዮን ከተማ፥ ኢየሩሳሌም ሆይ አትፍሪ!
እነሆ! ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” #ዘካ. 9፥9።
ተብሎ የተጻፈው ትንቢት እንዲፈጸም ነው።
16ደቀ መዛሙርቱ ይህ ነገር በመጀመሪያ አልገባቸውም ነበር፤ ግን ኢየሱስ በክብር ወደ ሰማይ ባረገ ጊዜ ይህ ነገር ስለ እርሱ እንደ ተጻፈና ለእርሱም እንደ ተደረገለት አስታወሱ።
17ኢየሱስ አልዓዛርን ከመቃብር በጠራውና ከሞት ባስነሣው ጊዜ አብረውት የነበሩ ሁሉ ስለ ኢየሱስ ይመሰክሩ ነበር። 18ብዙ ሰዎች ሊገናኙት የወጡትም ይህን ተአምር እንዳደረገ ሰምተው ስለ ነበር ነው። 19በዚህ ጊዜ ፈሪሳውያን፥ “እነሆ፥ የዓለም ሕዝብ ሁሉ ተከትሎታል! እኛ ምንም ማድረግ እንደማንችል ታያላችሁን?” ተባባሉ።
20በበዓሉ ጊዜ ሊሰግዱ ወደ ኢየሩሳሌም ከሄዱት ሰዎች መካከል፥ አንዳንድ ግሪኮች ይገኙ ነበር። 21እነርሱም ከገሊላ የቤተ ሳይዳ ሰው ወደ ሆነው ወደ ፊልጶስ ቀርበው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ኢየሱስን ማየት እንፈልጋለን” አሉት።
22ፊልጶስም ሄዶ ለእንድርያስ ነገረው፤ እንድርያስና ፊልጶስ አብረው ሄደው ለኢየሱስ ነገሩት። 23ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እነሆ፥ የሰው ልጅ የሚከበርበት ሰዓት ደርሶአል፤ 24እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ የስንዴ ቅንጣት በመሬት ወድቃ ካልሞተች፥ ብቻዋን ትቀራለች፤ ከሞተች ግን ብዙ ታፈራለች። #ማቴ. 10፥39፤ 16፥25፤ ማር. 8፥35፤ ሉቃ. 9፥24፤ 17፥33። 25ሕይወቱን የሚወድ ያጠፋታል፤ በዚህ ዓለም ሕይወቱን የሚጠላ ግን ለዘለዓለም ሕይወት ይጠብቃታል። 26እኔን ማገልገል የሚፈልግ ይከተለኝ፤ እኔ ባለሁበት አገልጋዬ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝንም አብ ያከብረዋል።”
ኢየሱስ ስለሚደርስበት መከራና ሞት መናገሩ
27ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እነሆ! ነፍሴ ተጨንቃለች፤ ምን ልበል? ‘አባት ሆይ! ከዚህች ሰዓት አድነኝ ልበልን?’ ይህን እንዳልል ግን እኔ የመጣሁት ለዚህች የመከራ ሰዓት ነው። 28አባት ሆይ! ስምህን አክብረው።”
ከዚህ በኋላ “ስሜን አክብሬዋለሁ፤ ደግሞም አከብረዋለሁ!” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።
29በዚያ የቆሙ ሰዎች ይህን በሰሙ ጊዜ፥ “ነጐድጓድ ነው!” አሉ። ሌሎች ደግሞ “መልአክ ነው የተናገረው!” አሉ።
30ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህ ድምፅ የመጣው ለእናንተ ሲል ነው እንጂ ለእኔ ሲል አይደለም፤ 31ይህ ዓለም የሚፈረድበት ጊዜ አሁን ነው፤ የዚህ ዓለም ገዢ ሰይጣን ወደ ውጪ የሚጣለው አሁን ነው፤ 32እኔም ከምድር ወደ ላይ ከፍ በተደረግሁ ጊዜ ሰውን ሁሉ ወደ እኔ አስባለሁ።” 33ኢየሱስ ይህን የተናገረው በምን ዐይነት ሞት እንደሚሞት ሲያመለክት ነበር።
34ሰዎቹም “በሕግ ተጽፎ የምናገኘው ‘መሲሕ ለዘለዓለም ይኖራል’ የሚል ነው፤ ታዲያ፥ አንተ፥ ‘የሰው ልጅ ወደ ላይ ከፍ ማለት አለበት’ እንዴት ትላለህ? ይህስ የሰው ልጅ ማን ነው?” አሉት። #መዝ. 110፥4፤ ኢሳ. 9፥7፤ ሕዝ. 37፥25፤ ዳን. 7፥14።
35ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም። 36የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃን እመኑ።” ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ ሄደና ተሰወረባቸው።
የአይሁድ አለማመን
37ኢየሱስም ብዙ ተአምራትን በፊታቸው ቢያደርግም እንኳ አይሁድ በእርሱ አላመኑም። 38ይህም የሆነው ነቢዩ ኢሳይያስ፥
“ጌታ ሆይ! ምስክርነታችንን ማን አመነ?
የጌታስ ኀይል ለማን ተገለጠ?” #ኢሳ. 53፥1።
ሲል የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው። 39እንደገናም ኢሳይያስ እንዲህ ሲል አለማመናቸውን ገለጠ፦
40“በዐይናቸው አይተውና
በልባቸው አስተውለው
እንዳይመለሱና እንዳይፈውሳቸው
እግዚአብሔር ዐይናቸውን አሳውሮአል፤
ልባቸውንም አደንድኖአል።” #ኢሳ. 6፥10።
41ኢሳይያስ ይህን ያለው የመሲሕን ክብር ስላየ ነው፤ ስለዚህ ይህን ስለ ኢየሱስ ተናገረ።
42ሆኖም ከአይሁድ አለቆች እንኳ ብዙዎቹ በኢየሱስ አምነዋል፤ ነገር ግን ፈሪሳውያን ከምኲራብ እንዳያስወጡአቸው በመፍራት፥ በግልጥ አልመሰከሩለትም። 43ይህንንም ያደረጉት ከእግዚአብሔር ከሚገኘው ክብር ይልቅ ከሰው የሚገኘውን ክብር ስለ ወደዱ ነው።
44ኢየሱስም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “በእኔ የሚያምን በእኔ ብቻ ሳይሆን፥ በላከኝም ያምናል፤ 45እኔን የሚያይ የላከኝን ያያል፤ 46በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ። 47ቃሌን ሰምቶ በሥራ ላይ የማያውለውን የምፈርድበት እኔ አይደለሁም፤ እኔ የመጣሁት ዓለምን ለማዳን ነው እንጂ በዓለም ላይ ለመፍረድ አይደለም። 48እኔን የማይፈልግና ቃሌንም የማይቀበለውን ሰው የሚፈርድበት አለ፤ እኔ የተናገርኩት ቃል በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል። 49እኔ በራሴ ሥልጣን አልተናገርኩም፤ እኔ የምለውንና የምናገረውን ትእዛዝ የሰጠኝ የላከኝ አብ ነው። 50የእርሱም ትእዛዝ የዘለዓለም ሕይወት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ። ስለዚህ እኔ የምናገረው አብ የነገረኝን ነው።”
Currently Selected:
የዮሐንስ ወንጌል 12: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: