መጽሐፈ ምሳሌ 6
6
ተጨማሪ ማስጠንቀቂያ
1ልጄ ሆይ! ዕዳውን ለመክፈል ለማይችል ሰው አንተ ልትከፍልለት ቃል ብትገባ፥ በተናገርከው ንግግር ብትጠመድ፥ 2በገባኸውም ቃል ብትያዝ፥ 3ልጄ ሆይ! በዚያ ሰው ሥልጣን ሥር ሆነሃል ማለት ነው፤ ስለዚህ ከእርሱ ቊጥጥር ነጻ ለመውጣት ብትፈልግ ፈጥነህ ወደ እርሱ ሂድ፤ ዋስትናውንም እንዲያወርድልህ ለምነው። 4ይህንን ሳታደርግ አትተኛ፤ በዐይንህም እንቅልፍ አይዙር። 5ሚዳቋ ከአዳኝ እጅ፥ ወፍ ከወጥመድ እንደሚያመልጡ አንተም ራስህን አድን።
6አንተ ሰነፍ ወደ ጒንዳን ሄደህ መንገድዋን ተመልክተህ ጥበብን ቅሰም። 7ጒንዳኖች መሪ፥ አለቃ፥ ወይም ገዢ የላቸውም፤ 8ነገር ግን በበጋ ወራት ምግባቸውን ያከማቻሉ፤ በመከር ጊዜ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ ይሰበስባሉ። 9ታዲያ፥ አንተ ሰነፍ! የምትተኛው እስከ መቼ ነው? ከእንቅልፍህስ የምትነቃው መቼ ነው? 10“ጥቂት እተኛለሁ፤ ጥቂት አንቀላፋለሁ፤ እጄንም አጣጥፌ ለጥቂት ጊዜ ዐርፋለሁ” ስትል፥ 11ገና ተኝተህ ሳለ ድኽነትና ማጣት የጦር መሣሪያ እንደ ታጠቀ ወንበዴ በድንገት ይደርሱብሃል። #ምሳ. 24፥33-34።
12ባለጌና ክፉ ሰው በየቦታው እየዞረ ነገር እያጣመመ ያወራል። 13እርሱም፥ ለማታለል በዐይኑ ይጠቅሳል፤ በእግሩ ያመለክታል፤ በእጁ ይጠቊማል። 14በጠማማ አእምሮው ዘወትር ክፉ ነገርን ለማድረግ ያቅዳል፤ ሁልጊዜ ጠብን ይዘራል። 15ስለዚህም በድንገት ጥፋት ይደርስበታል፤ ሊድን በማይችልበት ሁኔታ በቅጽበት ይወድማል።
16እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤ እንዲያውም እርሱ የሚጸየፋቸው ሰባት ሲሆኑ እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፦
17በንቀት የሚመለከት ዐይን፥
ሐሰትን የሚናገር ምላስ፥
ንጹሖች ሰዎችን የሚገድሉ እጆች፥
18ክፉ ሐሳብ የሚያፈልቅ አእምሮ፥
ወደ ክፋት ለመሮጥ የሚቸኲሉ እግሮች፥
19በውሸት ላይ ውሸት እየጨመረ የሚናገር ምስክር፥
በወዳጆች መካከል ጠብ የሚያነሣሣ ሰው።
ከአመንዝራነት ስለ መራቅ
20ልጄ ሆይ! የአባትህን ትእዛዞች ፈጽም፤ እናትህ ያስተማረችህንም ከቶ አትተው፤ 21የእነርሱን መመሪያ ዘወትር ተከተል፤ ቃላቸውንም ዘወትር ጠብቅ፤ 22እነርሱም በጒዞህ ይመሩሃል፤ ስትተኛም ይጠብቁሃል፤ ስትነቃም ያነጋግሩሃል። 23የእግዚአብሔር ትእዛዝ፥ እንደ መብራት፥ ትምህርቱም እንደ ብርሃን ያበሩልሃል፤ ተግሣጹ እንዴት መኖር እንደሚቻል ያስተምራል። 24ከመጥፎ ሴት እንድትርቅና ከሌላ ሰው ሚስት አሳሳች ቃል እንድትጠበቅ ይረዱሃል። 25ቊንጅናዋን አትመኝ፤ በዐይንዋ ጥቅሻ አትማረክ። 26አንድ ወንድ ሴትኛ ዐዳሪዋን በአንድ እንጀራ ዋጋ ሊያገኛት ይችላል፤ ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ማመንዘር ግን የሕይወት ዋጋ ያስከፍላል።
27በጉያው እሳት ይዞ ልብሱ የማይቃጠልበት ሰው አለን? 28እግሩስ ሳይቃጠል ፍም ረግጦ ለመሄድ የሚችል ሰው አለን? 29ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ግንኙነት የሚያደርግ እንደዚሁ ነው፤ የሌላውን ሰው ሚስት የሚነካ ሁሉ ሳይቀጣ አይቀርም። 30ሌባ በተራበ ጊዜ ምግብ ቢሰርቅ ለሰዎች አስገራሚ ነገር አይሆንም። 31ቢያዝም የቤቱን ሀብት ሁሉ የሚያሸጥ ቢሆን እንኳ ሰባት እጥፍ አድርጎ ይከፍላል። 32የምንዝር ተግባር የሚፈጽም ሰው ግን ማስተዋል የጐደለው ነው፤ ሕይወቱንም በከንቱ ያጠፋል። 33ውርደትና ድብደባ ይደርስበታል፤ ሁልጊዜም እንደ ተዋረደ ይኖራል። 34ቅናት የባልን ቊጣ ያነሣሣል፤ በሚበቀልበትም ጊዜ አይራራም። 35ምንም ዐይነት ካሳ መቀበል አይፈልግም፤ የስጦታም ብዛት ቊጣውን አያበርድለትም።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 6: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: