መጽሐፈ መዝሙር 101
101
ንጉሥ ለእግዚአብሔር የሚገባው ቃል ኪዳን
1እግዚአብሔር ሆይ!
ስለ ታማኝነትህና ስለ ትክክለኛ ፍርድህ እዘምራለሁ፤ አዜማለሁም።
2ነቀፋ የሌለበት ሕይወት እኖራለሁ፤
ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው?
ከቤተሰቤ ጋር በቅንነት እኖራለሁ።
3ክፉ ነገር ሲደረግ አይቼ ዝም አልልም፤
ከእግዚአብሔር የራቁ ሰዎች የሚያደርጉትን ሁሉ እጠላለሁ፤
ከቶም አልተባበራቸውም።
4ጠማማ ልብ ያላቸው ሰዎች ከእኔ ይራቁ፤
ከክፋትም ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም።
5ሰውን በሹክሹክታ የሚያማውን ሰው ዝም አሰኛለሁ፤
ትዕቢተኛ ዐይንና ትምክሕተኛ ልብ ያለውን ሰው አልታገሠውም።
6ለእግዚአብሔር ታማኞች የሆኑትን እመርጣለሁ፤
አገልጋዮቼም በሕይወታቸው ነቀፋ የሌለባቸው ይሆናሉ።
7አታላይ ሰው በቤቴና
ሐሰትን የሚናገር በእኔ ዘንድ አይኖርም።
8በምድሪቱ የሚገኙትን ክፉዎች ሰዎች በየዕለቱ ጸጥ አሰኛለሁ፤
ከእግዚአብሔርም ከተማ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ አጠፋለሁ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 101: አማ05
Highlight
Share
Copy
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fen.png&w=128&q=75)
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: