YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 16

16
የእግዚአብሔርን አለኝታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
1አምላክ ሆይ!
የምታመነው በአንተ ስለ ሆነ ጠብቀኝ፤
2እግዚአብሔርን “አንተ ጌታዬ ነህ፤
ያለኝ መልካም ነገር ሁሉ
ያንተ ስጦታ ነው” አልኩት።
3በምድር ላይ የሚኖሩ ቅዱሳን
የተከበሩ ናቸው፤
በእነርሱም እደሰታለሁ።
4ሌሎች አማልክትን የሚያመልኩ
ብዙ ሐዘን ይደርስባቸዋል፤
እኔ እንደነዚህ ላሉት አማልክት የደም መሥዋዕትን አላቀርብም፤
እነርሱንም አላመልክም።
5እግዚአብሔር ሆይ! ዕድል ፈንታዬና ጽዋዬ አንተ ነህ፤
ድርሻዬንም አስተማማኝ ታደርገዋለህ።
6ለእኔ የተለኩልኝ የድንበር መስመሮች ያረፉት በሚያስደስቱ ቦታዎች ላይ ነው፤
በእርግጥ እኔ የሚያስደስት ርስት አለኝ።
7የሚመክረኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤
በሌሊት እንኳ ሕሊናዬ ያስተምረኛል።
8ዘወትር እግዚአብሔርን አስቀድማለሁ፤
እርሱም በቀኜ ስለ ሆነ አልታወከም።
9ስለዚህ ልቤ ተደስቶ ይፈነጥዛል፤
ሰውነቴም ያለ ስጋት ያርፋል።
10ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤
ታማኝህንም መበስበስ እንዲደርስበት አታደርግም። #ሐ.ሥ. 13፥35።
11የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤
በአንተ ፊት ሙሉ ደስታ፥
በቀኝህም የዘለዓለም እርካታ ይገኛል። #ሐ.ሥ. 2፥25-28።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for መጽሐፈ መዝሙር 16