መጽሐፈ መዝሙር 19
19
ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ክብር ይገልጣል
1ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤
የሰማይ ጠፈርም፥ የእጁን ሥራ ያውጃል።
2አንዱ ቀን ለሌላው ቀን ያንኑ መልእክት ያስተላልፋል፤
አንዱም ሌሊት ለሌላው ሌሊት ዕውቀቱን ያካፍላል።
3ንግግር ወይም ቃላት የላቸውም፤
ድምፃቸውም አይሰማም፤
4ነገር ግን መልእክታቸው ወደ ዓለም ሁሉ ይሠራጫል፤
እስከ ምድር ዳርቻም ይደርሳል፤
እግዚአብሔር የፀሐይን መኖሪያ በሰማይ አደረገ። #ሮም 10፥18።
5ሙሽራ ከጫጒላ ቤት እንደሚወጣ ፀሐይ ብሩህ ሆኖ ይወጣል፤
ሯጭ በሩጫ ውድድር እንደሚደሰትም ደስ ይለዋል።
6ከአንዱ የሰማይ ዳርቻ ተነሥቶ
ወደ ሌላው የሰማይ ዳርቻ ይገሠግሣል፤
ከሙቀቱም ኀይል ሊደበቅ የሚችል ምንም ነገር የለም።
የእግዚአብሔር ሕግ
7የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤
ለነፍስ አዲስ ሕይወትን ይሰጣል፤
የእግዚአብሔር ትእዛዝ የታመነ ነው፤
ማስተዋል ለጐደላቸው ጥበብን ይሰጣል።
8የእግዚአብሔር ሕግ ትክክል ነው፤
ለልብ ደስታን ይሰጣል፤
የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤
ለዐይን ብርሃንን ይሰጣል።
9እግዚአብሔርን መፍራት ለዘለዓለም የሚኖር ንጽሕና ነው፤
የእግዚአብሔር ፍርዶች ሁሉ እያንዳንዳቸው እውነትና ጽድቅ ናቸው።
10እነርሱ ከንጹሕ ወርቅ የበለጠ ዋጋ ያላቸው ናቸው፤
ከማር ወለላ ይበልጥ ጣፋጮች ናቸው።
11እንዲሁም አገልጋይህ በእነርሱ ይመከራል፤
እነርሱንም በመጠበቅ ታላቅ ዋጋ ያገኛል።
12የራሱን ስሕተት የሚያይ ማንም የለም፤
አምላኬ ሆይ! ከተሰወረ በደል አንጻኝ።
13ኃጢአት እንዳይሠለጥንብኝ ዐውቆ ከመበደል ጠብቀኝ፤
ይህም ከሆነ ታላቅ በደል ከመሥራት ንጹሕ እሆናለሁ።
14አምባዬና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ!
ቃላቴና ሐሳቦቼ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ይኑራቸው።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 19: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 19
19
ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ክብር ይገልጣል
1ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤
የሰማይ ጠፈርም፥ የእጁን ሥራ ያውጃል።
2አንዱ ቀን ለሌላው ቀን ያንኑ መልእክት ያስተላልፋል፤
አንዱም ሌሊት ለሌላው ሌሊት ዕውቀቱን ያካፍላል።
3ንግግር ወይም ቃላት የላቸውም፤
ድምፃቸውም አይሰማም፤
4ነገር ግን መልእክታቸው ወደ ዓለም ሁሉ ይሠራጫል፤
እስከ ምድር ዳርቻም ይደርሳል፤
እግዚአብሔር የፀሐይን መኖሪያ በሰማይ አደረገ። #ሮም 10፥18።
5ሙሽራ ከጫጒላ ቤት እንደሚወጣ ፀሐይ ብሩህ ሆኖ ይወጣል፤
ሯጭ በሩጫ ውድድር እንደሚደሰትም ደስ ይለዋል።
6ከአንዱ የሰማይ ዳርቻ ተነሥቶ
ወደ ሌላው የሰማይ ዳርቻ ይገሠግሣል፤
ከሙቀቱም ኀይል ሊደበቅ የሚችል ምንም ነገር የለም።
የእግዚአብሔር ሕግ
7የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤
ለነፍስ አዲስ ሕይወትን ይሰጣል፤
የእግዚአብሔር ትእዛዝ የታመነ ነው፤
ማስተዋል ለጐደላቸው ጥበብን ይሰጣል።
8የእግዚአብሔር ሕግ ትክክል ነው፤
ለልብ ደስታን ይሰጣል፤
የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤
ለዐይን ብርሃንን ይሰጣል።
9እግዚአብሔርን መፍራት ለዘለዓለም የሚኖር ንጽሕና ነው፤
የእግዚአብሔር ፍርዶች ሁሉ እያንዳንዳቸው እውነትና ጽድቅ ናቸው።
10እነርሱ ከንጹሕ ወርቅ የበለጠ ዋጋ ያላቸው ናቸው፤
ከማር ወለላ ይበልጥ ጣፋጮች ናቸው።
11እንዲሁም አገልጋይህ በእነርሱ ይመከራል፤
እነርሱንም በመጠበቅ ታላቅ ዋጋ ያገኛል።
12የራሱን ስሕተት የሚያይ ማንም የለም፤
አምላኬ ሆይ! ከተሰወረ በደል አንጻኝ።
13ኃጢአት እንዳይሠለጥንብኝ ዐውቆ ከመበደል ጠብቀኝ፤
ይህም ከሆነ ታላቅ በደል ከመሥራት ንጹሕ እሆናለሁ።
14አምባዬና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ!
ቃላቴና ሐሳቦቼ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ይኑራቸው።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997