መጽሐፈ መዝሙር 43
43
የስደት ጊዜ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! ፍረድልኝ፤
በአንተ ከማያምኑ አሕዛብ ፊት
ስለ እኔ ተከራከርልኝ፤
ከአታላዮችና ከክፉ ሰዎችም እጅ አድነኝ።
2አንተ አምላኬ፥ ጠንካራ ምሽጌ ነህ፤
ታዲያ፥ ስለምን ትተወኛለህ?
ለምንስ ጠላቶቼ እያበሳጩ ያሳዝኑኝ?
3ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤
እነርሱ እየመሩ ወደ ተቀደሰው ተራራህ፥
ወደ ማደሪያ መቅደስህም ያምጡኝ።
4አምላክ ሆይ! ከዚያም በኋላ ለአንተ ለምታስደስተኝ
ወደ መሠዊያህ ሄጄ እሰግድልሃለሁ፤
አንተ አምላኬ ነህ፤
በገናዬን እየደረደርኩ አመሰግንሃለሁ።
5እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ?
ለምንስ እጨነቃለሁ?
በእግዚአብሔር እተማመናለሁ።
ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 43: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 43
43
የስደት ጊዜ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! ፍረድልኝ፤
በአንተ ከማያምኑ አሕዛብ ፊት
ስለ እኔ ተከራከርልኝ፤
ከአታላዮችና ከክፉ ሰዎችም እጅ አድነኝ።
2አንተ አምላኬ፥ ጠንካራ ምሽጌ ነህ፤
ታዲያ፥ ስለምን ትተወኛለህ?
ለምንስ ጠላቶቼ እያበሳጩ ያሳዝኑኝ?
3ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤
እነርሱ እየመሩ ወደ ተቀደሰው ተራራህ፥
ወደ ማደሪያ መቅደስህም ያምጡኝ።
4አምላክ ሆይ! ከዚያም በኋላ ለአንተ ለምታስደስተኝ
ወደ መሠዊያህ ሄጄ እሰግድልሃለሁ፤
አንተ አምላኬ ነህ፤
በገናዬን እየደረደርኩ አመሰግንሃለሁ።
5እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ?
ለምንስ እጨነቃለሁ?
በእግዚአብሔር እተማመናለሁ።
ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997