YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 93

93
እግዚአብሔር ንጉሥ ነው
1እግዚአብሔር ንጉሥ ነው፤
ግርማንና ኀይልን ተጐናጽፎአል፤
ምድርን በአንድ ስፍራ አጸናት፤
ከቶም አትናወጥም።
2እግዚአብሔር ሆይ! ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤
አንተም ከዘመናት ሁሉ በፊት አምላክ ነህ።
3እግዚአብሔር ሆይ! ባሕሮች ይነሣሉ፤
ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤
የሞገዳቸውም ድምፅ ይሰማል።
4ነገር ግን ድምፁ ከብዙ ውቅያኖሶች ድምፅ ይልቅ ታላቅ የሆነው
ከባሕር ማዕበሎችም የበረታው እግዚአብሔር፥
ከሁሉ የበለጠ ኀያል ነው።
5እግዚአብሔር ሆይ! ሕግህ ጽኑ ነው፤
መቅደስህም ለዘለዓለም ያማረና ቅዱስ ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in