መጽሐፈ ሩት መግቢያ
መግቢያ
ሰላም የሰፈነበት የሩት ታሪክ የተገኘው በመጽሐፈ መሳፍንት በተገለጠው የዐመፅ ጊዜ ነው፤ የሞአብ አገር ተወላጅ የሆነችው ሩት ለአንድ እስራኤላዊ ሰው ተድራ ነበር፤ ባልዋ በሞተ ጊዜ ሩት እስራኤላዊ ለሆነችው ምራቷ እጅግ አስደናቂ የሆነ ታማኝነት ታሳያታለች፤ እንዲሁም ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር ያድርባታል፤ በመጨረሻም ከድሮ ባልዋ ዘመዶች መካከል አንድ ሌላ ሰው ታገባለች፤ በዚህም ጋብቻ አማካይነት የእስራኤል ታላቅ ንጉሥ ለነበረው ለዳዊት ቅድመ አያት የመሆንን ዕድል ትጐናጸፋለች።
በመጽሐፈ መሳፍንት ያሉት ታሪኮች የእግዚአብሔር ሕዝብ ከእግዚአብሔር በመራቃቸው የደረሰባቸውን ጥፋት ያሳያሉ፤ በመጽሐፈ ሩት ያለው ታሪክ ደግሞ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ፊቷን የመለሰች አንዲት ባዕድ ሴት የምታገኘውን በረከትና ታማኞች ከሆኑት ሕዝቡ መካከል አንዷ ልትሆን መብቃቷን ያሳያል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የናዖሚ ከሩት ጋር ወደ ቤተልሔም መመለስ 1፥1-22
የሩትና የቦዔዝ መገናኘት 2፥1—3፥18
ቦዔዝ ሩትን ማግባቱ 4፥1-22
Currently Selected:
መጽሐፈ ሩት መግቢያ: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: